የሩሲያ ነዳጅ በግሪክ ባህር አድርጎ ከመርከብ መርከብ እየተዟዟረ ወደ አውሮፓ ከተሞች እየገባ ነው ተብሏል
የሩሲያ ነዳጅ በድብቅ ወደ አውሮፓ ገበያዎች እየገባ እንደሆነ ተገለጸ።
ሩሲያ ለልዩ ዘመቻ በሚል ጦሯን ወደ ዩክሬን ማስገባቷን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት በሞስኮ ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።
ማዕቀብ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል የሩሲያ ነዳጅ ወነኛው ሲሆን ሩሲያም ማዕቀቡ ካልተነሳ አንድም ጠብታ ነዳጅ ወደ አውሮፓ እንደማትልክ አስታውቃለች።
ይሁንና አውሮፓ በነዳጅ እጥረት እየተፈተነች ሲሆን ችግሩን ለመፍታት በሚል ነጋዴዎች በህገወጥ መንገድ የሩሲያን ነዳጅ ወደ አውሮፓ ከተሞች እያጓጓዙ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ነዳጅ አከፋፋዮች የሩሲያን ነዳጅ ከሩሲያ ወደ ግሪክ በመርከብ በማምጣት እና ከግሪክ ባህር በሌላ መርከብ ወደ አውሮፓ ከተሞች እያጓጓዙ ነው ተብሏል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 147 መርከቦች 24 ሚሊዮን ብር ምን የሩሲያን ነዳጅ ከመርከብ ወደ መርከብ አጓገዘዋል።
የአውሮፓ ህብረት ከሚቀጥለው የካቲት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የሩሲያን ነዳጅ ላለመግዛት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ሩሲያ የእስያ ሀገራትን ዋነኛ የነዳጇ ሸማቾች ለማድረግ እየሰራች መሆኗን አስታውቃለች።
ይሁንና የአውሮፓ ሀገራት በነዳጅ እጥረት እየተፈተኑ ሲሆን ዜጎቻቸውም የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እንዲደረጉላቸው በስራ ማቆም አድማ እየጠየቁ ይገኛሉ።
የፈረንሳይ እና ጀርመን የአቪዬሽን ባለሙያዎች ከአንድ ወር በፊት ባካሄዱት የስራ ማቆም አድማ እያንዳንዳቸው ከአንድ ሺህ በላይ በረራዎችን መሰረዛቸው አይዘነጋም።