ሩሲያ በዩክሬኗ የወደብ ከተማ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን ባለስጣናት ተናገሩ
ይህ ጥቃት ሞስኮ በተከታታይ በከተማዋ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች ወዲህ ከባድ የሚባል ነው ተብሏል
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ለፈጸመችው አረመኔያዊ ጥቃት ከዩክሬን ጦር ተገቢውን ምላሽ ታገኛለች ሲሉ ዝተዋል
ሩሲያ በዩክሬኗ የወደብ ከተማ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን ባለስጣናት ተናገሩ
ሩሲያ በዩክሬኗ የወደብ ከተማ ኦደሳ ላይ ባደረሰችው የሚሳይል ጥቃት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ75 በላይ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ለፈጸመችው አረመኔያዊ ጥቃት ከዩክሬን ጦር ተገቢውን ምላሽ ታገኛለች ሲሉ ዝተዋል።
ይህ ጥቃት ሞስኮ በተከታታይ በከተማዋ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች ወዲህ ከባድ የሚባል መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የግዛቱ አስተዳዳሪ ኦሌህ ኪፐር በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት በሩሲያ ቁጥጥር ስር ካለችው ክሬሚያ የተተኮሱ ሁለት ኢስካንደር-ኤም ሚሳይሎች በንጹሃን መኖሪያ ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
በዚህ ጥቃት ምክንያት ጥቂት ነዋሪዎች የጋዝ እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቆት ተቋርጦባቸዋል ብለዋል አስተዳዳሪወ።
ኪፐር "ፍንዳታው በተለይም ሁለተኛው በጣም ከባድ ነበር... ይህ ከክሬሚያ የተተኮሰ ኃይለኛ ሚሳይል ነው" ብለዋል።
ኪፐር እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች እና የነፍስ አድን ሰራተኞች በሁለተኛው ሚሳይል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው "ለሩሲያ ገዳዮች ምላሽ ለመስጠት የዩክሬን ጦር የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል" ሲሉ ዝተዋል።
የደቡብ ዩክሬን ወታደራዊ እዝ በጥቃቱ አንድ በለሶስት ፎቅ ህንጻ እና 10 የግል ቤቶች መውደማቸውን ገልጿል።
በምስራቅ ዩክሬን ያሉ አራት ግዛቶችን በከፊል የተቆጣጠረችው ሩሲያ ሙሉ በሙሉ ለመያዝ ከባለፈው ወር ጀምሮ ከፍተኛ ጥቃት በመክፈት አቭዲቪካን ጨምሮ በርካታ መንደሮችን መቆጣጠር ችላለች።
ዩክሬን በበኩሏ ወሰኝ የተባለችውን አብዲቪካን ሌሎች መንደሮችን ለቃ የወጣችው የምዕራባውያን የጦር መሳሪያ እርዳታ በቶሎ ባለመድረሱ ነው የሚል ምክንያት ማቅረቧ ይታወሳል።