አቃቤ ህግ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮንን ጨምሮ በ62 ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ
ከፌደራል መንግስት ከ8 ወር በኋላ መከላከያን ከትግራይ ማስቀጣቱ ይታወሳል
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ህወሓት ሀገረመንግስትን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር ተሳትፋል በሚል በሽብርተኝነት ፈርጆታል
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ባወጣው መግለጫ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑትን ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ በሌሎች በ62 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል፡፡
ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህወሓት)አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፤ ውሳኔ በመስጠት ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው የህውሀት መዓከላዊ ኮሚቴ አባላትና የክልል መንግስቱ ካቢኔ አባላት መሆናቸውን አቃቤ ህግ ግልጿል፡፡
በትጥቅ ጥቃት ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢፈርት ድርጅቶች፣ የግልና የመንግስት ድርጅት አመራሮች፣ የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አመራር አባላት፣ በትግራይ በተካሄደው ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ምርጫ ላይ ተሳትፎ ያደረጉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ክስ ተመስርቶበቸዋል ብላል መግለጫው፡፡
ክሱ የተመሰረተው በሁለት የወንጀል አንቀጽ ስር ሲሆን የመጀመሪያው በሀይል በዛቻ በአድማና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ኢ-ሕገመንግስታዊ ምርጫ በማካሄድ በሕገ-መንግስት የተቋቋመና እውቅና ያለው የክልል መንግስት መለወጥ የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ነው ብሏል
መግለጫው በሁለተኛ ክስ የፌዴራሉን መንግስት በሀይል ለመለወጥ በማሰብ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል መንግስትን በመሳሪያ ጥቃት መለወጥ የሚችል የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ የተባለ የጦር ሀይል አደራጀተዋል በሚል ነው፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለክሱ አስረጅነት 510 የሰው ምስክሮችን እና እና 5329 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎችን በማያያዝ ለፍርድ ቤቱ ቅርቧል፡፡
ግጭቱ ከተጀመረ ከ8 ወራት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተከስ አቁም አውጆ፤ መከላከያ ሰራዊትን ከትግራይ ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ህወሓት ሀገረመንግስትን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር ተሳትፋል በሚል በሽብርተኝነት መፈረጁ ይታወሳል፡፡