የፌደራል መንግስትና ህወሓት የፊታችን ሰኞ በደቡብ አፍሪካ እንደሚደራደሩ ተገለጸ
አምባሳደር ሬድዋን ድርድሩ የፊታችን ጥቅምት 14 እንደሚካሄድ አፍሪካ ህብረት አሳውቆናል ብለዋል
የፌደራል መንግስት እና የህወሓት ድርድር ከሁለት ሳምንት በፊት በሎጂስቲክስ ምክንያት መራዘሙ ይታወሳል
የፌደራል መንግስት እና ህወሀት የፊታችን ሰኞ በደቡብ አፍሪካ እንደሚደራደሩ ተገለጸ።
የአፍሪካ ህብረት ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲመጣ የፌደራል መንግስትን እና ህወሀትን ለማደራደር ቦታ ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል።
የህብረቱን ድርድር ሁለቱም ወገኖች በወቅቱ መቀበላቸውን ያሳወቁ ቢሆንም ዘግይቶ በወጣ መረጃ ደግሞ ድርድሩ በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙ አይዘነጋም።
የጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት የአፍሪካ ህብረት የፌደራል መንግስት እና ህወሀት በደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ድርድር የፊታችን ሰኞ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥቅምት 24/2022 እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
አምባሳደር ሬድዋን አክለውምየፌደራል መንግስት ድርድሩን እንደተቀበሉ ገልጸው የተወሰኑ አካላት ሀሰተኛ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሀት ጥቅምት 2013 ዓ. ም በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መማድረሱን ተከትሎ ነበር ጦርነቱ የተጀመረው።
በዚህ ጦርነት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለእርዳታ ሲዳረግ በቢሊዮን የሚቆጠር ንብረት ደግሞ ወድሟል።