አረብ ኤሚሬትስ በኮረሮና ወረርሺኝ ጉዳይ ለአፍሪካ ትልቅ ድጋፍ ማድረጓን የአፍሪካ ህብረት ገለጸ
ህብረቱ ከአቡ ዳቢ የጤና ወኪሎች ኤጀንሲ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም በመጨረሻ ምእራፍ አንደሚገኝም አስታውቋል
አፍሪካ ኮሮናን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ዩኤኢ ለአፍሪካ ሀገራት የተለያዩ የቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጓ የሚታወስ ነው
የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በኮረሮና ወረርሺኝ ጉዳይ ለአፍሪካ ትልቅ ድጋፍ ማድረጓ የአፍሪካ ህብርት ገለጸ፡፡
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (Africa CDC) ምክትል ዳይሬክተር አህመድ ኦግዌል ኦውማ (ዶ/ር) ከአል-ዐይን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ፤ የኮሮና ወረርሺኝ ወደ አፍሪካ ከገባበትና ከስተስፋፋበት ጊዜ አንስቶ ህብረቱ ከዩኤኢ ጋር በተለያዩ መስኮች ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
- ኢትዮጵያ በኤሚሬትስ የሲቪል ተቋማት ላይ የደረሰውን “የሽብር ጥቃት”አወገዘች
- ኤሚሬትስ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ12 ሀገራት ላይ የጣለችውን የጉዞ እግድ ከቅዳሜ ጀምሮ ልታነሳ ነው
ወረርሺኙ እንደተስፋፋ በነበሩ መጀመሪያ ጊዜያት ከየግል መከላከያ መሣሪያዎች እና ማስኮች ጋር በተያያዘ የነበረውን ችግር በማቃለል ዩኤኢ ትልቅ ሚና እንደነበራትም ነው ያነሱት ምክትል ዳይሬክተሩ፡፡
ዳየአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (Africa CDC) አሁንም ቢሆን ከዩኤኢ ጋር እንደ መረጃ መለዋወጥ እና የተቋማት አቅምን ማጎልብት በመሳሰሉ የትብብር ማእቀፎች በጋራ እየሰራ መሆኑን አንስቷል፡፡
“ከአቡ ዳቢ የጤና ወኪሎች ኤጀንሲ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም በመጨረሻ ምእራፍ ላይ እንገኛለን”ም ነው ያሉት፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ “አፍሪካን ተጠቃሚ ለማድረግ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያላትን የማኑፋክቸሪንግ የክትባት አቅም እንዴት መጠቀም እንደምንችል እየተነጋገርን ነው” ሲሉም አክሏል፡፡
አፍሪካ አሁን ያላት ሁሉም ዓይነት ክትባቶችን የማምረት አቅም 1 በመቶ ብቻ የሚሸፍን ነው ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ እንደፈረንጆቹ በ2040 የማምረት አቅም ወደ 60 በመቶ ከፍ ለማድረግ እንደ ዩኤኢ ከመሳሰሉ ሀገራት በትብብር መስራት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
“እኛ 1.3 ቢልዮን ህዝብ ነው፤ ትልቅ ገባያ ነን ማለት ነን ስለዚህም ምን ማምረት አለብን በሚል ጉዳይ ላይ እርግጠኛ ከሆንን በኋላ የማምረት አቅማችን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ እንችላለንም ሲሉም ነው የተናገሩት የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል ምክትል ደይሬክተር አህመድ ኦግዌል ኦውማ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አፍሪካ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ያላትን ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡