በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ላይ በኢትዮጵና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ዙሪያ የኢትዮጵያ አቋም ምን ነበር?
37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጉዳይን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን ተመልክቷል
በጉባዔው በኢትዮጵና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ጉዳይ በሶማሊያ መነሳቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥታለች
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኀብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ አመርቂ ተሳትፎ እንደነበራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ መጠናቀቁን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታዎች አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና አምባሰደር ምስጋኑ አርጋ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታአምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኢትዮጵያ በጉባዔው በነበራት ተሳትፎ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ አመርቂ ተሳትፎ እንደነበራት ገልጸዋል።
በጉባዔው ላይ በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኢትዮጵያን በሚመለከት በተለይም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ሪፖርት መቅረቡን እና በበጎ የታየ መሆኑን አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ ስኬት ያስመዘገበችበት ጉዳይ የአፍሪካ የንግድ ቀጠናን የተመለከተ ነው ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ሚኒስትሮች በተካሄደ ስብሰባ ላይ የሸቀጦች ዋጋ ዝርዝር በማቅረብ በመሪዎች ደረጃ አጸድቃለች ብለዋል።
ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንግድ ቀጠናን የሸቀጦች ንግድ መጀመር ከሚችሉ ሀገራተ ዝርዝር ውስጥ መግባታቷን ነው አምባሳደር ምስጋኑ ያስታወቁት።
በኢትዮጵና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት
የሶማሊያ መንግስት በተለይም በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነትን የተመለከቱ ጉዳዮች በመሪዎች ደረጃ መነሳቱን አምባሳደር ምስጋኑ አስታውቀዋል።
“ኢትዮጵያ በዋነኛነት በቀጠናው የኢኮኖሚ ውህደት፣ ትስስርና ትብብር ለመፍጠር የምትሰራ ሀገር ናት” ያሉት ሚኒስትሩ፤ “ለጎረቤቶቻችን ችግር ሆነንን አናውቅም ወደፊትም ችግር አንሆንም” ብለዋል።
“የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋኛነት በትብብር፣ በሰጥቶ መቀበል፣ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ነው” ያሉት አምባሳደር ምስጋኑ፤ “የሌሎች ሀገራትን የግዘት አንድነት የማከበር ችግር ኖሮብን አያውቅም” ሲሉም ገልጸዋል።
“ኢትዮጵያ የየትኛውን ሀገር ግዝት ገንጥላም፤ አስገንጥላም፣ ወስዳም ይሂን ወራ አታውቅም” ብለዋል አምባሳደር ምስጋኑ።
በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ላይም የሶማሊያ መንግስት ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ ከፍ አድርገው በሚያነሱበት ልክ አለመሆኑን ኢትዮጵያ ምለሽ መስጠቷን ነው ሚኒስትር አዴታው ያስታወቁት።
“ይልቁንም በስምምነቱ ኢትዮጵያ የአካባቢውን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም በትብብር ላይ የተመሰረተ ልማት ልናመጣ እንደምንችል ያሳየንበት ነው” ብለዋል
“ሶማሊያ ስምምነቱ ችግር አለው ብላ የምታስብ ከሆነ ኢትዮጵያ ሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ለጉባዔው አሳውቃለች” ሲሉም ገልጸዋል።
“የሶማሊያ መንግስት ይህንን አጀንዳ ከፍ በማድረግ የራሳቸውን የውስጥ ድክመት ለመሸፈን እየተጠቀሙበት” እንደሆነ አምባሳደር ምስጋኑ አስረድተዋል።
በተያያዘ ዜና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በጉባኤው ላይ በጊዜያዊነት ከህብረቱ ከተገዱ ሃገራት በስተቀር ሁሉም አባል ሀገራት መሳተፋቸውን ና 31 የሀገራት በመሪዎች ደረጃ በጉባኤው መሳተፋቸውን ገልፀዋል።
ከ8 ሺህ በላይ የውጭ እንግዶች በጉባኤው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የጠቀሱት አምባሳደር ብርቱካን፤፥ ከ500 በላይ የውጭ ሚድያ ባለሙያዎች ፍቃድ አግኝተው መሳተፋቸውንም በመግለጫው ላይ አንስተዋል።
ከ200 በላይ መደበኛ በረራዎች ሳይስተጓጎሉ ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ 54 ቻርተር በረራዎችን በቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ማስተናገድ ተችሏል ብለዋል።