የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ወደ አፍሪካ ህብረት ስብሰባ እንዳልገባ ለመከልከል ተሞክሯል” ብለዋል
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ በራሳቸው እና በልኡካቸው ላይ ደርሷል ስላሉት መጉላላት ላይ የኢትዮያ መንግስት ምለሽ ሰጠ።
37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን፤ የሶማያሊው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃድ ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ የመከልከል ሙከራ እንደተደረገባቸው አስተውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከስብሰባው መክፈቻ በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ በዝግ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በሚሞክሩበት ጊዜ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ካረፉበት ሆቴል እንዳይወጡ መንገድ ዘግተው እንደከለከሏቸው ገልጸዋል።
“በሌላ ፕሬዝዳንት መኪና ከሆቴል በመውጣት የስብሰባው ስፍራ ብደርስም፤ የፀጥታ አካት እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብን ነበር ብለዋል” ፕሬዝዳቱ በመግለጫቸው።
በኋላ ላይ ግን ፕሬዝዳንቱ ወደ ስብሰባው መግታቸው እና በስብሰባው መክፈቻ እንዲሁም የቤተሰብ ፎቶ ላይም ታይተዋል።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ላይ በሰጠው መግለጫውም፤ “የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ልኡካቸው ወደ 2024 የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንዳይገቡ ያደረገውን ሙከራ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት በጽኑ ያወግዛል” ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ደንብን የሚጥቀስ ነው ያለው የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የአፍሪካ ኅብረትን የቆየ ባህል የሚቃረን በመሆኑ ህብረቱ ጉዳዩን በገለልተኛ ሆኖ እንደሚረምርም ጠይቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠʔ
አል ዐይ ኒውስ በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ባገኘው ምላሽ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታት መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ማድረጉን አስታውቋል።
እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታቸው ደህንነታውን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበትም አስታውቋል።
ነገር ግን የሶማሊያ ፕሬዝዳት ልኡካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም ማለታቸውን ነው አል ዐይን ኒውስ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ያገኘው መግለጫ ያመለክታል።
ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደህንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት መከልከላቸውን ገልጿል።
በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማያው ፕሬዝዳንት እና የልኡካቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ እንዳላደናቀፈ እንዲሁም ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊዜ እንዳይገቡ እንዳልከለከለ አሳውቋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም ነው የመንስት ኮሙዩኒኬሽን መግለጫ የሚያመላክተው።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለው የፈረንጆቹ ጥር አንድ ቀን በፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ ምክንያት ቁጣቸውን ያሰሙት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ የፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሰጥታ በምላሹ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባህር ጠረፍ በ50 አመት የሊዝ ኪራይ እንድታገኝ የሚያስችል መሆኑ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።
ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አካል አድርጋ የምታያት ሶማሊያ በስምምነቱ ከፍተኛ ቁጣ በማሰማት ከአምባሳደሯን ከኢትዮጵያ መጥራቷም አይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም ብለዋል።