አፍሪካ ህብረት፤ የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ወደነበረበት እስኪመለስ ድረስ ካርቱም ታግዳ እንደምትቆይ አስታወቀ
የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ተወካዮቻቸውን ወደ ሱዳን በመላክ ለንግግር መደላድል እንዲፈጥሩም ተጠይቋል
ህብረቱ ጦሩ ያሰራቸውን ሁሉንም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ አሳስቧል
የአፍሪካ ህብረት ሱዳን ሪፐብሊክ በየትኞቹም የድርጊት መርሃ ግብሮቹ እንዳትሳተፍ አገደ፡፡
ህብረቱ እገዳው የሽግግር ሂደቱን ይመራ የነበረው የሲቪል አስተዳደር ወደ ቦታው እስከሚመለስ የሚቀጥል ነው ብሏል፡፡
ካርቱም በህብረቱ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ፕሮቶኮል አንቀጽ 7 መሠረት ነው የታገደችው እንደ ህብረቱ ገለጻ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የሚመራው የሱዳን የሲቪል መንግስት በሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሚመራው የሃገሪቱ ጦር ከስልጣን መወገዱ ይታወሳል፡፡
የአፍሪካ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የተጣሉ ማእቀቦች እንዲነሱ ጠየቀ
በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተነሱት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከእስር ተለቀቁ
ሃገሪቱን ከእርስበእርስ ጦርነት ለመታደግ በሚል እርምጃውን መውሰዳቸውን የገለጹት ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሃምዶክ የሚመራውን የሲቪል መንግስት ጨምሮ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱ እንዲሁም ሌሎች የሙያ ማህበራት መበተናቸውን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
የጦሩ ይህን ማድረግ እጅግ አሳስቦኛል ያለው ህብረቱም ሁኔታው ሃገሪቱን ዳግም ወደ ግጭት ሊያስገባት እንደሚችል በማሳሰብና የጦሩን ስልጣን መያዝ በጽኑ በማውገዝ ኢ-ህገመንግስታዊ እና ተቀባይነት የሌለው ነው በሚል ባለ 11 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብን አውጥቷል፡፡
ጠ/ሚ አብደላ ሃምዶክን የለቀቀው ጦሩ በእስር ላይ ያሉትን ሁሉንም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲለቅና መብቶቻውን እንዲያከብር በማሳሰብ ምክር ቤቱ ወደነበረበት ስልጣን እስኪመለስ ድረስ ካርቱም ከአባልነት ታግዳ እንደምትቆይ አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የተጣሉ ማእቀቦች እንዲነሱ ጠየቀ
በጉዳዩ ላይ ከሁሉም አካላት ጋር ለመነጋገር መወሰኑን ያስታወቀም ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጁባ የሰላም ስምምነትን ጨምሮ ከአሁን ቀደም ለተደረሱ ስምምነቶች ተግባራዊነት ቁርጠኛ እንዲሆኑና ጦሩ በኃላፊነቱ ብቻ እንዲወሰን ጥሪ አቅርቧል፡፡
ሁሉም አካላት ከጸብ አጫሪ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እንዲሁም የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ተወካዮቻቸውን ወደ ሱዳን በመላክ ለንግግር መደላድል እንዲፈጥሩ ጠይቋል፡፡