የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው አለ
“በሱዳን የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ የውጭ ተዋናዮች ጣልቃገብነት አያስፈልግም” ብሏል
የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሱዳን ህዝብ ጎን እንደሚቆሙም አስታውቋል
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቷል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ፤ ሱዳን ሕዝብ ሉዓላዊ ምኞቶች እንዲከበሩ ጽኑ ፍላጎት እንዳላት አስታውቋል።
አዲስ አበባ በካርቱም ፖለቲካ የውጭ ተዋናዮች ጣልቃ እንዳማያስፈልግም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን የተከናወኑትን ክስተቶች በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለጸው መግለጫው ይህም በሁለቱ ሀገሮች ሕዝቦች መካከል ለዘመናት ካለው ጠንካራ የወንድማማች ትስስር የመነጨ እንደሆነም አትቷል፡፡
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሲመሰረት የኢትዮጵያ መንግስት በማስታረቅና የሽግግሩን ዘመን ህገ መንግስታዊ ሰነድ እውን በማድረጉ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱንም አስታውሷል መግለጫው።
የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ሰላምና መረጋጋትና መረጋጋት እንዲኖር እንዲሁም ይህ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቆም ሁሉንም ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያ የሱዳን ሕዝብ ሉዓላዊ ምኞቶች እንዲከበሩ ፍላጎት እንዳላት የገለጸች ሲሆን የውጭ ተዋናዮች በሱዳን የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ አለመግባታቸውን አስፈላጊነት እንደሆነ እምነቷ መሆኑን ገልጻለች።
የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሱዳን ህዝብ ጎን እንደሚቆምም ገልጿል።