ፖለቲካ
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የዩክሬን ኪቭ ግዛት ጎበኙ
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት፤ በተለይም በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል
ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ "አውስትራሊያ በዬክሬን ላይ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ፍትህ እንዲሰጥ ትፈልጋለች" ብለዋል
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ በዩክሬን ኪቭ ግዛት ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በኪቭ ግዛት ውስጥ በጦርነት የተጎዱ ሶስት ከተሞችን መጎብኘታቸውም የግዛቱ አስተዳዳሪ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የግዛቱ አስተዳዳሪ ኦሌክሲ ኩሌባ በቴሌግራም ላይ እንደጻፉት “የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒሰትር አልባኒዝ ቡቻ፣ ኢርፒን እና ሆስቶሜል የተባሉትን ከተሞች ጎብኝተዋል” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጎብኝታቸው በኋላ "አውስትራሊያ ዩክሬንን ትደግፋለች እናም እዚህ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ፍትህ እንዲሰጥ ትፈልጋለች" ሲሉ ተናግረዋል።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት፤ በተለይም በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በቅርቡ እንኳን በገበያ ማዕከል ላይ የተፈጸመውና በርካቶችን ህይወት የነጠቀው አስደንጋጭ ጥቃት በሩሲያ ኃይሎች መፈጸሙ ሚታወስ ነው።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ፤ ዩክሬን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ውስጥ ታይቶ የማያውቅ 'ጭካኔ' እያጋጠማት ነው ማለቱ አይዘነጋም።