የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት በኤክስ ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ አነሳ
ፍርድ ቤቱ በኤክስ ላይ እግድ የጣለው የአሳይሪያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ሲወጉ የሚያሳይውን ቨዲዮ ለማጥፋት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር
የአውስትራሊያ ባለስጣናት በጳጳሱ ላይ የደረሰውን ጥቃት የሽብር ጥቃት ሲሉ ፈርጀውታል
የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት በኤክስ ወይሞ ትዊተር ሲባል በነበረው የማህበራዊ ገጽ ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ አስነስቷል።
የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት ንብረትነቱ የአሜሪካው ቢሊዮነር ኢሎን መስክ በሆነው የኤክስ ኩባንያ ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ እንዲያራዝም በሀገሪቱ የሳይበር ደህንነት ተቆጣጣሪ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
ፍርድ ቤቱ በኤክስ ላይ እግድ የጣለው የአሲሪያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ማር ማሪ ኢማኑኤል ሲወጉ የሚያሳይውን ቨዲዮ ለማጥፋት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር።
የአውስትራሊያ ባለስጣናት በጳጳሱ ላይ የደረሰውን ጥቃት የሽብር ጥቃት ሲሉ ፈርጀውታል።
የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ጆፈሪ ኬንት ባለፈው ወር የተጣለው እግድ እንዲራዘም የቀረበው ማመልከቻ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል።
ዳኛው ውድቅ የተደረገበት ምክንያት ይፋ እንደሚደረግ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል። ጉዳዩ በመጭው ረቡዕ እንዲታይ የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል።
የህግ ክርክሩ መስክን ትዕቢተኛው ቢሊየነር ሲሉ በጠሩት የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ በሌሎች ባለስጣናት እና ቪዲዮውን ለማውረድ ፍቃደኛ ባልሆነው መስክ መካከል የኃይለቃል ምልልስ እንዲነሳ አድርጓል።
መስክ ቪዲዮውን እንዲያወርድ በተቆጣጣሪው የቀረበውን ጥያቄ የሀሳብ ነጻነትን ይጋፋል በሚል ነበር ያልተቀበለው። ሌሎች የሜታ ፕላትፎርሞች ግን ሲጠየቁ ወዲያውኑ አጥፍተውታል።
በአውስትራሊያ ሁለተኛው የሆነው የፌደራል ፍርድ ቤት ባለፈው ወር ኢሴፍቲ ኮሚሽኘር አገልግሎት እየሰጡ የነበሩ ጳጳስ በቢለዋ ሲወጉ የሚያሳዩ 65 ቪዲዮዎች ለግጭት የሚያነሳሱ በመሆናቸው እንዲነሱ ሲል ያስተላለፈውን ውሳኔ ተቀብሎት ነበር።
ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው የ16 ታዳጊ ወንድ ልጅ የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።
የአውስትራሊያ ተመልካቾች ፖስቶቹን እንዳያዩ ተደርገው የነበረ ቢሆንም መስክ በመላው አለም እንዳይታይ ለማድረግ ወይም ጨርሶ ለማጥፋት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።
ተቆጣጣሪው ባለፈዉ ሳምንቱ ለፍርድ ቤቱ እንደተናገረው ኤክስ በጂኦ-ብሎኪንግ ወይም በአውስትራሊያ ውስጥ እዳይታይ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም ሩብ የሚሆነው ህዝብ ያሉበትን ቦታ በመደበቅ ቨርቹዋል ፕራይቤት ኔትወርክ ስለሚጠቀም ውጤታማ አልሆነም።