የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር መስክን "ትዕቢተኛው ቢሊየነር" ሲሉ ተቹ
መስክ የጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ መንግስትን የሀሳብ ነጻነትን በመገደብ ወይም በሴንሰርሺፕ ከሷል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመስክ ላይ ትችት የሰነዘሩት በቤተክርስያን ውስጥ የተፈጸመውን በስለት የመውጋት አደጋ የሚያሳየውን ቪዲዮ ከኤክስ ገጽ ለማንሳት ቸልተኝነት በማሳየቱ ነው
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ አሜሪካዊውን ኢለን መስክን "ትዕቢተኛው ቢሊየነር" ሲሉ ተችተውታል።
መስክ በአውስትራሊያ ሲዲኒ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን በስለት የመውጋት አደጋ የሚያሳይ ቪዲዮ ከኤክስ ገጽ ለማጥፋት ቸልተኝነት በማሰየቱ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ትዕቢኛው ቢሊየነር" ብለው የጠሩት።
ባለፈሰ ሰኞ እለት የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት ኤክስ ወይም ቀደም ሲል ትዊተር የሚባለው የመስክ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያ የሲዲኒውን የቤተክርስቲያን ጥቃት የሚያሳየውን ቪዲዮ እንዲደብቀው ወይም ከእይታ እንዲሰውረው ውሳኔ አሳልፏል።
መስክ የጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ መንግስትን የሀሳብ ነጻነትን በመገደብ ወይም በሴንሰርሺፕ ከሷል።
ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መስክ "ከህግ በላይ ብቻ ሳይሆን ከሞራላዊ ጨዋነት በላይ ነኝ ብሎ ያስባል" ብለው መናገራቸውን ቢቢሲ ኤቢሲ የተባለውን የቴሌቫዥን ጣቢያ ጠቅሶ ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት የአውስትራሊያ ኢሴፍቲ ኮሚሽነር ኤክስ እና ሌሎች ማህበራዊ ገጸች በአሳይሪያ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን እና ፖሊስ የሽብር ድርጊት ሲል የጠራውን የመውጋት አደጋ የሚሳየውን ቪዲዮ ካላጠፉ ከባድ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቆ ነበር።
ኤክስ የአውስትራሊያ ህግ ይህን ትዕዛዝ ማስተላለፍ አይችልም የሚል መከራከሪያ ሲያቀርብ ቆይቷል።
ኮሚሽነሯ ኤክስ ከአውስትራሊያ ውጭ ያሉ ተጠቃሚዎች ቪዲዮውን እንዲያዩት ስላደረገ ፍርድ ቤት እግድ እንዲጥል ጠይቀዋል።
"ኤክስ በህግ አለመገዛቱ እና ለመከራከር መሞከሩ አስገርሞኛል" ሲሉ አልባኔዝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
መስክ በጠቅላይ ሚኒስትሩም ይሁን በኮሚሽነሯ የቀረበበትን ትችል አይቀበለውም።
ኮሚሽነር ጁሊ ኢንማንን "የአውስትራሊያ የሴንሰሬሽፕ ኮሚሽነር" ሲል ነው መስክ የተቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ ኢንማን አውስትራሊያውያንን እየጠበቁ ነው ሲሉ ተከላክለዋል።
ሰኞ እለት የተጣለው እግድ ሁለተኛው የፍርድ ቤት ክርክር እስከሚሰማበት ርብዕ ድረስ ይቆያል ተብሏል።