ዩክሬን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ግዙፍ የተባለ የድሮን ጥቃት ሩሲያ ላይ ፈጽማለች
ከተጀመረ 1 ሺህ 53ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የሩሲያ ክሬን ጦርነት አሁንም ተባብሶ ቀጥሎ ይገኛል።
የሩሲያ ጦር አሁንም አዳዲስ ቦታዎችን መቆጣጠሩን የቀጠለ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም በዶኔስክ ክልል የሚገኝ ታይሞፊቭካ የተባለ መንደር መቆጣጠሩን የሩሲያ የዜና አግልግሎን የሀገሪቱን የመከላያ ሚኒስቴር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ዩክሬን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሩሲያ እጅ ሊወደቁ የተቃረቡ 16 መንደሮች ውስጥ የሚገኙ 267 ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው አካባውን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።
ኪቭ በሩሲያ ጦር የተያዙ እና ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ 6 የዩክሬን ወታደሮች ተገድለዋል ስትል ከሳለች።
ሩሲያ በምስራቅ እና በማእለዊ ዩክሬን በድሮን እና በሚሳዔል በፈጸመቻቸው ጥቃቶች የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተነግሯል።
የሩሲያ ጦር ከዩክሬን የተነሱ ከ120 በላይ ድሮኖችን አየር ላይ እያሉ ማምከኑን ያስታወቀ ሲሆን፤ ዶሮኖቹ ዋና ከተማዋ ሞስኮን ጨምሮ የተለያዩ የሩሲያ ግዘቶችን ኢላማ ያደረጉ ነበር ብሏል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ዩክሬን አሁን ላይ ያደረገችው የድሮን ጥቃት ሙከራ በአይነቱ እና በመጠኑ ግዙፉ ነው ተብሎለታል።
የሩሲያዋ ራይዛን ክልል አስተዳዳሪ ሰርጊ ሶብያኒን፤ የሩሲያ ጦር የአየር መከላከያ ክፍል ወደ ሞስኮ ሲያቀኑ የነበሩ ሶስት ድሮኖችን አየር ላይ መትቶ መጣሉን እና የወደቁ ድሮኖች ምንም አደጋ አለማስከተላቸውን ተነግረዋል።
ሩሲያም በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ማድረጓም የተነገረ ሲሆን፤ የዩክሬን ጦር ከሩሲያ ከተላኩ 97 ድሮኖች ውስጥ 57 ድሮኖችን አየር ላይ መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
የሩሲያ መከላያ ሚኒስቴር በበኩሉ በ3 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከዩክሬን የተላኩ 49 ድሮኖችን አየር ላይ መትቶ መጣሉን ገልጿል።
ከእነዚህም ውስጥ 37 የዩክሬን ድሮኖች ውጊያ እየተደረገበት ባለው የሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ውስጥ ተመትተው መውደቃቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።