ፖለቲካ
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በ1 ሺህ 53ኛ ቀኑ ምን አዳዲስ ክስተቶችን አስተናግዷል?
የሩሲያ ጦር በማእከላዊ ፖክሮቭስክ የሚገኝ ሼቭቼንኮ የተባለ ስፍራ ተቆጣጥሯል
ዩክሬን ከተተኮሱባት 56 የሩሲያ ድሮኖች 46 ማክሸፏን አስታውቃለች
ከተጀመረ 1 ሺህ 53ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የሩሲያ ክሬን ጦርነት አሁንም ተባብሶ ቀጥሎ ይገኛል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫው በቀጠለው ጦርነት የሩሲያ ጦር አዳዲስ ስፍራዎችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ብሏል።
በዚህም የሩሲያ ጦር በዩክሬን ወሳኝ የሎጂስቲክ ማዕከል በሆነችው ፖክሮቭስክ አቅራቢያ የሚገኝ ሸቭቼንኮ የተባለች መንደርን ተቆጣጥሯል።
የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ዶኔስክ ክልል ቁልፍ ቦታዎችን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ግስጋሴ መቀጠሉንም የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዩክሬን በበኩሏ ከሩሲያ የሚተኮሱ ድሮች አሁንም ቀጥለዋል ያለች ሲሆን፤ የዩክሬን ጦር አዛዥ ከሩሲያ ከተተኮሱ 56 ድሮኖች ውስጥ 46 ድሮኖችን አክሽፈናል ብለዋል።
ዩክሬን ወደ ሩሲያ በላከችው ድሮን ደግሞ ግዙፍ የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ መምታቷ ተነግሯል፤ ተመታው የነዳጅ ማጣሪያ በታራስታን ታኔኮ የሚገኝ ነው።
በሩሲያ ኩርስክ ክልል እየተደረገ ባለው ውጊያ ሁለት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን መማረኳንም ዩክሬን አስታውቃለች።
ዬክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፤ የደቡብ ኮሪያ ብሔራዊ የስለላ አገልግሎት ለሀገራቸው ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።