የቀድሞውን ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር መሀሪን ከኃላፊነት ለማንሳት የተሰጠውን ምክንያት ዶ/ር መሀሪ እንደማይስማሙበት ገልጸዋል
የቀድሞውን ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ዶ/ር መሀሪን ከኃላፊነት ለማንሳት የተሰጠውን ምክንያት ዶ/ር መሀሪ እንደማይስማሙበት ገልጸዋል
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከኃላፊነት በተነሱት የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶ/ር መሀሪ ታደሰ ቦታ አዲስ ምክትል ከንቲባ መሾሙን አስታውቋል፡፡
አስቸኳይ ጉባኤው የጠራው የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክርቤት የአዲሱን ከንቲባ ሹመት አጽድቋል፡፡አዲስ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ድረስ ሳህሉ መሆናቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
የአማራ ክልል መንግስት ዶ/ር ማህሪ ፈቃድ ጠይቀው ወደ ውጭ መሄዳቸውንና በተባለው ጊዜ ባለመመለሳቸው ምክንያት ከኃላፊነት መነሳታቸውን ገልጿል፡፡
ነገርግን ዶ/ር መሀሪ የክልሉ መንግስት 2 ወር ቀን ከ15 ቀን ውጭ ቆዩ የሚለውን ክስ እንደማይቀበሉት በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸው ነበር፡፡
ዶ/ር መሀሪ በውጭ በነበሩት ጊዜም የባህርዳር ከተማን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ እንደነበር መጻፋቸው ይታወሳል፡፡