“አማራ ክልል፤ ኦሮሚያ ክልል… ስትሄድ እንትና ታሰረ…” -ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ
“አማራ ክልል፤ ኦሮሚያ ክልል…ስትሄድ እንትና ታሰረ…”-ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “እናንተ ደግሞ ሻል ባለው አለም ያላችሁ ሕግ ይከበር በሉ እንጅ፣ ወንጀል ያልሰራ ሰው ነጻነት ይኑረው በሉ እንጅ የኔ ወገን አትበሉ” ሲሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተደምጠዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ሰሞኑን ወደ መካከለኛው ምስራቅ በማቅናት፣ በዚያ ከሚኖሩ 300 ከሚሆኑ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች(ዩኤኢ) በተወያዩበት ወቅት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
“ወንጀለኛ ወገን የለውም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አማራ ክልል ስትሄድ እንትና ታሰረ፣ ኦሮሚያ ክልል ስትሄድ እንታና ታሰረ፤ ያንተ መንግስት ኦሮሞን እያሰረ ነው ይላሉ ሲዳማ ስተሄድ…. ሁሉም ያራሱን አጉልቶ ያነሳል” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ብዙውን እየነካን አይደለም ነገርግን በዚህ አለመግባባት እንዳለ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመካከኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መብት ከማስከበር አንፃር ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ፣ አንደ ዩኤኢ ያሉ ሀገራት ጋር የሚስተካከል አቅም ባይኖረንም “የሚገደልና ረጅም ጊዜ የሚታሰረ ሰው ካል” በዜጋ ተኮር ፖሊሲያችን ትኩረት እንሰጣለን ብለዋል፡፡
“ይህ ሀገር (ዩኤኢ) ያሉት ውስን ዜጎች ናቸው፤ በሰው ሀገር እንዲዋረዱ አይፈልግም፡፡”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “አንድ ዩኤኢ ዜጋ በአሜሪካ ሆነ በእንግሊዝ ወይንም በየትኛውም ቦታ ትንሽ ችግር ቢያጋጥመው ምንያህል ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ትገምታላችሁ፡፡”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመካከለኛው ምስረቅ ቆይታቸው ፣ ኑሮቸውን በዚያ ካደረጉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ያካሂዳሉ ተብሏል፡፡