የሩሲያ የቅርብ አጋር የሆነችው ቤላሩስ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠጋች
መከላከያ ሚኒስትሩ ቤላሩስ የድንበሯን መጣስ እንደትንኮሳ እንደምታየው እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነች ገልጸዋል
የዩክሬን ድሮኖቸ የአየር ክልሏን እንደጣሱባት የገለጸችው ቤላሩስ ተጨማሪ ወታደሮችን ከዩክሬን ወደምትዋሰንበት ድንበር ልካለች
የሩሲያ የቅርብ አጋር የሆነችው ቤላሩስ ጦሯን ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠጋች።
የዩክሬን ድሮኖቸ የአየር ክልሏን እንደጣሱባት የገለጸችው ቤላሩስ ተጨማሪ ወታደሮችን ከዩክሬን ወደምትዋሰንበት ድንበር ልካለች።
የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬንን አምባሳደር ተወካይ መጥራቱን እና እንዲህ አይነት ተግባር ድጋሚ እንዳይከሰት እርምጃዎች እንዲወሰድ መጠየቁ ተገልጿል። ዩክሬን በድጋሚ የአየር ክልል የምትጥስ ከሆነ ቤላሩስ የኪቭ የዲፕሎማቲክ ተልእኮ በሚኒስክ የመኖር "አስፈላጊነትን" ልታጤነው እንደምትችል ሚኒስቴሩ አመላክቷል።
ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሸንኮ በምስራቅ ቤላሩስ በተካሄደ ስብሰባ ላይ እንደናገሩት የአየር መከላከያው ከበርካታዎቹ የዩክሬን ድሮኖች ውስጥ "በደርዘን የሚቆጠሩትን" የቤላሩስን ድንበር ከጣሱ በኋላ ከሩሲያ ጋር በሚያዋስነው ሞግሊቭ ግዛት መትቶ ጥሏል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን የቅርብ አጋር ከሆኑት አንዱ የሆኑት ሉካሸንኮ ሌሎቹ ቆየት ብለው በሩሲያዋ ያሮስሌቭል ከተማ አቅራቢያ ተመተው ወድመዋል ብለዋል።
"ዩክሬን ለምን ይህን እንደምታደርግ አላውቅም። በጥልቀት እናየዋለን" ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ቤልቲኤ የተባለውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጠቅሶ ዘግቧል።
"ነገርግን ግልጽ ማድረግ የምንፈልገው እና ለእነሱ ማሳወቅ የምንፈልገው ለማንኛውም ትንኮሳ ምላሽ እንደሚሰጥ ነው" ብለዋል ሉካሸንኮ።
ቤላሩስ ዋን የተባለው የቤላሩስ የመንግስት ቴሌቪዥን የድሮን ስብርባሪ ያሳያል ያለውን ቪዲዮ አሳይቷል።
የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለቤልቲኤ ቴሌቪዥን ሚኒስክ እንዲህ አይነት ድርጊት እንዳይደገም ግልጽ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ትፈልጋለች ሲሉ ተናግረዋል።
የዩክሬን የጸረ-የተሳሳተ መረጃ ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አንድሪ ኮቫለንኮ ግን ቤላሩስ በድንበር አካባቢ የወታደር ቁጥር የምትጨምረው ሩሲያን ለመርዳት ነው ብለዋል።
በዩክሬን እና በሩሲያ ኩርስክ ግዛት ያለውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥ እንዲህ አይነት ትንኮሳዎች ቢከሰቱ በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት ታክቲካል በሆኑት ጎሜል እና ሞዚር ግዛቶች ተጨማሪ ወታደሮች እንዲሰማሩ ማዘዙን የመከላከያ ሚኒሰትሩ ቪክቶር ክሬኒን ተናግረዋል።
መከላከያ ሚኒስትሩ ቤላሩስ የድንበሯን መጣስ እንደትንኮሳ እንደምታየው እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነች ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የዩክሬን ወታሮች ባልተጠበቀ ሁኔታ ኩርስክ ወደተባለው የሩሲያ ግዛት መግባታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል።