የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው እንደሚወዳደሩ አስቀድመው መናገራቸው ይታወሳል
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሁለተኛ ጊዜ በፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ተገለጸ።
አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ያሉት ጆ ባይደን በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ላይ ዳግም ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከአንድ ወር በኋላ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
- ጆ ባይደን “ጽንፈኛ” ያሏቸውን ዶናልድ ትራምፕንና ደጋፊዎቻቸውን አስጠነቀቁ
- ዶናልድ ትራምፕ “ጆ-ባይደን አሜሪካን እያዋረዳት ስለሆነ በ2024 ድጋሚ ለምርጫ ልወዳደር እችላለሁ” አሉ
የ80 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ባይደን ከሶስት ዓመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕን በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ዳግም በምርጫው ተወዳድረው ካሸነፉ እና የፕሬዝዳንት ዘመናቸው ሲያልቅ 86 ዓመት ይሞላቸዋል።
ይህም በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ታሪክ በእድሜ ትልቁ ወይም አዛውንቱ ፕሬዝዳንት እንደሚያስብላቸው ተገልጿል።
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረዳቶች እንዳሉት ፕሬዝዳንቱ በያዝነው ሳምንት ኬንተኪን ከኦሂዮ የሚያገናኘው ድልድይ ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ስለቀጣይ የምርጫ ዘመቻቸው እንደሚናገሩ ፍንጭ ሰጥተዋል።
የፕሬዝዳንት ባይደን የምንጊዜም ተቀናቃኛቸው የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚወዳደሩ መናገራቸው ይታወሳል።