ጆ ባይደንና ኬንያታ በትግራይ ተጨማሪ ህይወት እንዳይጠፋ በመከላከል አስፈላጊነት ላይ ተወያዩ
መሪዎቹ በሌሎች ቀጣናዊ የሰላም ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንም መግለጫው ጠቅሷል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ክልል ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ መከላከል አስፈላጊነት ላይ ከኬንያወኡሁሩ ጋር ተወያዩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ክልል ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ መከላከል አስፈላጊነት ላይ ከኬንያው ኡሁሩ ጋር ተወያዩ
ኋይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከኬንያው አቻቸው ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በስልክ መወያየታቸውን አስታውቋል፡፡መሪዎቹ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መጥቷል ባሉት የሰብአዊና ሰብአዊ መብት ቀውስ እንዲሁም በክልሉ ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ በመከላከል አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች ከዚህ ባለፈም በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍን ማረጋገጥ እንደሚገባም መነጋራቸውን ኋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
መሪዎቹ ዋሸንግተንና ናይሮቢ ያላቸውን ሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን ኋይት ሀውስ ገልጿል፡፡ጆ ባይደን የኬንያ መንግስት አመራር በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በመከላከል፣በኢኮኖሚ ዕድገትና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ላሳየው ውጤት ስራ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መሪዎቹ በሌሎች ቀጣናዊ የሰላም ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውንም መግለጫው ጠቅሷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከካናዳ አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር በሀገራዊ እና ቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ትናንት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡