ፕሬዝዳንት ባይደን ዩክሬን ወደ ኔቶ ለመግባት የምታደርገው ጥረት ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው አሳሰቡ
አሜሪካና ኔቶ ለዩክሬን አባልነት ሳይሆን ድጋፍ ብቻ እንደሚሰጡ ተገልጿል
በኔቶ ጉባዔ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አባል ለመሆን ምን መደረግ እንዳለበት እንዲገነዘቡ ይደረጋል ተባለ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ብሪታኒያ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ የጀመሩት የሦስት ሀገራት ጉብኝት በሊትዌኒያ በሚካሄደው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ ኪየቭ ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለችው ውጊያ አጋርነታቸውን ለማሳየት ነው ተብሏል።
አጋርነቱ ድጋፍ እኔጂ ዩክሬን የኔቶ ህብረት አባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት እንደማይኖረው ተነግሯል።
በዚህ ሳምንት በሊትዌኒያ ከሚካሄደው የጥምረቱ ጉባኤ በፊት በባይደን እና በቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን መካከል በተደረገው የስልክ ልውውጥ በኔቶ 31 አባል ሀገራት መካከል ያለው አብሮነት ተግዳሮቶች ጎልተው ታይተውበታል።
ባይደን ሰኞ ምሽት ወደ ቪልኒየስ፤ ሊቱዌኒያ ተጉዘው ማክሰኞና ረቡዕ ከኔቶ መሪዎች ጋር ይወያያል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ባይደንና የኔቶ አጋሮች ዓላማ ለዩክሬን ድጋፍ ለማሳየት እና የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የኔቶ አባልነትን ለማግኘት ወደ ፊት ምን መደረግ እንዳለበት እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው።
ፕሬዝዳንቱ በኔቶ የጋራ መከላከያ ስምምነት መሰረት ጥምረቱ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ጉዞውን በተመለከተ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል።
ለአሁኑ ዩክሬን ወደ ኔቶ ለመግባት የምታደርገው ጥረት ጥንቃቄ እንደሚሻም አሳስበዋል።
"አሁን በጦርነት መሀል ዩክሬንን ወደ ኔቶ ቤተሰብ ለማድረጋት እና ላለማድረግ በኔቶ ውስጥ አንድነት ያለ አይመስለኝም" ብለዋል።
ዘለንስኪ ዩክሬን ወደ ኔቶ እንድትቀላቀል መጋበዙ የምዕራቡ ዓለም መከላከያ ጥምረት ሞስኮን እንደማይፈራ መልዕክት እንደሚያስተላልፍም ተናግሯል።
ዩክሬን በኔቶ ውስጥ ባይሆንም እንኳ ግልጽ የሆነ የደህንነት ዋስትናዎችን ማግኘት አለባት ሲሉም አክለዋል።