ዩክሬን በሩሲያ ላይ የፈጸመችው ግዙፍ የድሮን ጥቃት ምን ያክል ጉዳት አስከተለ?
ዪክሬን ጦርነቱ ከተጀመረ ወደሂህ በታሪክ ግዙፍ የተባለውን የድሮን ጥቃት ሩሲያ ላይ ፈጽማለች

ዩክሬን 337 ድሮኖችን ተጠቅማ ጥቃት የፈጸመች ሲሆን፤ 91 ድሮኖች ሞስኮን ኢላማ እድርገዋል
ዩክሬን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በመጠኑ ከፍተኛ ነው የተባለ የድሮን ጥቃት በሩሲያ ላይ መፈጸሟ ተነግሯል።
ዩክሬን በሩሲያ ላይ በፈጸመችው መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ቢያነስ 3 ሰዎች ሲሞቱ፤ 18 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተነግሯል።
ዩክሬን በ337 ድሮኖች ሩሲያ ላይ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 91 ድሮኖች ሞስኮን ኢላማ ያደረጉ እንደነበሩ የሩሲያው የዜና ኤጀንሲ ታስ ባወጣው መረጃ ያመለክታል።
የሞስኮ ክልል አስተዳዳሪ አንድሪ ቨሮብዮቭ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ በተፈጸመው ጥቃት በርታ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል።
በመቶዎች በሚቆጠሩ ድሮኖች በተፈጸመው ጥቃትም በርካታ ህንጻዎች መጎዳቸውን እና በሞስኮ የሚገኝ ኤርፖርት ዝግ መዘጋታቸውን እና የባር ትንስፖር መቋረጡን አስታውቀዋል።
የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጊ ሶብያን በበኩላቸው፤ “የጠላት ድሮኖች በሞስኮ ላይ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ፈጽመዋል፤ የሩሲያ አየር ኃይል ጥቃቶቹን አየር ላይ አምልክኗል” ብለዋል።
ከንቲባው አክለውም በሞስኮ ከተማ ብቻ 7 የመኖሪያ አፓርትምት ህንጻዎች በድሮኖች ስብርባሪ መጎዳታቸውን አስታውቀዋል።
በሞስኮ ሶስት ህጻናትን ጨምሮ 12 ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰም ነው ከንቲባው ያስታወቁት።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የድሮን ጥቃቶቹን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ ሌሊት ላይ ሞስኮን ኢላማ ያደረጉ 91 ድሮኖችን ጨምሮ 337 የድሮን ጥቃቶችን አየር ላይ ማምከኑን አስታውቋል።
የዪክሬን የብሄራዊ ደህንነት ቢሮ ባለስልጣን የሆኑት አንድሪይ ኮቫሌንኮ፤ በታሪክ ከፍተኛ የሆነ የድሮን ጥቃት በሩሲያ ላይ ተፈጽሟል ብለዋል።
“የድሮን ጥቃቱ የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረሱ ጫና ለማድረግ የታሰባ ነው” ሲሉም ተናግዋል።
ሩሲያ ባሳለፍነው ሳምት አርብ ከዩክሬን ላይ የፈረንጆቹ 2025 ከገባ ወዲህ ግዙፍ የተባለ የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟ ይታወሳል።
ሩሲያ በፈጸመቻቸው መጠነ ሰፊ ጥቃች 25 ሰዎች መሞታውን ዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።