ሩሲያ 2025 ከገባ ወዲህ በዩክሬን ላይ ከባድ የተባለውን ጥቃት ፈጸመች
ሩሲያ ከጦር መርከብ ላይ የተተኮሱ 20 ሚሳዔሎችን ጨምሮ በ58 ሚሳዔሎችና 194 ድሮኖችን ተጠቅማ ጥቃት ፈጽማለች

የሩሲያ ጦር ዶኔትስክ ክልል ውስጥ የሚገኘውን አንድሪቪካ መንደር መያዙን አስታውቋል
ሩሲያ የፈረንጆቹ 2025 ከገባ ወዲህ በዩክሬን ላይ ከባድ የተባለውን ጥቃት መፈጸሟ ተነገረ።
በጥቁር ባህር ላይ የተሰማሩ የጦር መርከቦችን ባሳተፈው መጠነ ሰፊ ጥቃት ሩሲያ 58 ሚሳዔሎችን እና 194 ድሮኖችን ተጠቅማ ጥቃቱን ሰንዘራለች።
ሩሲያ በዩክሬን በፈጸመችው መጠነ ሰፊ ጥቃት ቢያንስ አራ ህጻናትን ጨምሮ18 ሰዎች ቆስለዋል የተባለ ሲሆን፤ የሰው ህይወት ስለማፉ ግን የወጣ ሪፖርት የለም ተብሏል።
የዩክሬን ባህር ኃይል ቃል አቀባይ ዲሜትሮ ፕሌቴንቸክ ከሀገሪቱ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሩሲያ የፈረንቹ 2025 ከተጀመረ ወዲህ በጥቁር ባህር ላይ የተሰማሩ የጦር መርከቦችን ያሳተፈ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሰንዝራለች ብለዋል።
በጥቁር ባህር ላይ የተሰማሩ የጦር መርከቦች አዳሩን ብቻ ከ20 በላይ ሚሳዔሎችን ወደ ዩክሬን መተኮሳቸውን አስታውቀዋል።
የዩክሬን አየር ኃይል በበኩሉ ሩሲያ አዳሩን በአጠቃላይ 58 ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን ተጠቅማ ጥቃት ሰንዝራለች።
አየር ኃይሉ 34 ሚሳኤሎች እና 100 ድሮኖችን ኢላማቸውን ሳይመቱ አየር ላይ መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
የሩሲያን መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመከላከለወም የፈረንሳይ ሚራጅ ተዋጊ ጄቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማሰማራቱን ገልጿል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳታወቀው ከሆነ የሩሲያ ኃይሎች በትናንትው እለት ምሽት ዶኔትስክ ክልል ውስጥ የሚገኘውን አንድሪቪካ መንደር መያዛቸውን አስታውቋል።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ጦርቱን በሰላም ስምምነት ለመቋጨት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ለማስቆም ቃል በገቡት ትራምፕ የሚመራው የአሜሪካ አስተዳደር ከሩሲያ ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል።