
3 ዓመት የሞላውን ጦርነት ለማቆም ጥረቶች እየተደረጉ ባሉበት ሰዓት ውጊያው ተባብሶ ቀጥሏል
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሀገሪቱ ጦር በዩክሬን ካርኪቭ ክልል የሚገኝ መንደር መቆጣጠሩን አስታውቋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ የሩሲያ ኃይሎች ካርኪቭ ክልል የሚገኝ ቶፖሊ የተባለ አንድ መንደር መቆጣጠራቸውን ገልጿል።
በ24 ሰዓታ ውስጥም የሩሲያ ኃይሎች ከዩክሬን ጦር በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈተበትን ጥቃቶች መመከቱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
በዛሬው እለትም በዩክሬን ወታደራዊ አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት መፈፀሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋ።
በዚህም የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን ማምረቻዎች መመታቸውን እና 905 የሚደርሱ የየዩክሬን ጦር አባላት መሞታውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ውጊው አሁን በተለያዩ ግንባሮች ተጠናክሮ ንደቀጠለ አስታውቋ።
የዩክሬን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እንደተናገሩት በትናናው እለት ብቻ በ69 የተለያዩ በግንባሮች ውጊዎች መካዳቸው አስታውቀዋል።
የዩክሬን ጦር በካርኪፍ አቅጣጫ በሩሲያ ጦር የተከፈተበትውጊያ በመመከት በኩፒያንስክ፣ ፖክሮቭስክ እና ኩርስክ አቅጣጫዎች ላይ ጥቃት መሰንሩን አስታውቀዋል።
በተያያዘ ባለፉት 24 ሰዓታት ዩክሬን ከሩሲያ የተተኮሱ 6 ሚሳዔሎችን እና 133 ድሮኖችን መት መጣሉት አስታውቃለች።
ሩሲያ 7 ሚሳዔሎችን እንደተኮች እና 213 ድሮኖችን እንደላከች ያስታወቀው የዩክሬን ጦር
ከ133 ድሮኖች በተጨማሪ ስድስቱ ሚሳኤሎች አየር ላይ ተመትተው ወድቀዋል ያለው የዩክሬን አየር ኃይል፤ 79 ድሮኖች ደግሞ ኢላማቸው ላይ መድረስ አልቻሉም ብሏል።
በፈረንጆቹ የካቲት 24 2022 የተጀመረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በትናትው እለት 3ኛ ዓመቱን ደፍኗል።
በዩክሬን ላይ "ልዩ ያለችውን ዘመቻ" በ2022 የከፈተችው ሩሲያ ዶኔስክንና ሌሎች በከፊል የያዘቻቸውን ሶስት ግዛቶች የራሷ ግዛት አድርጋ አውጃለች። ይህ የሩሲያ እርምጃ በተባበሩት መንግስት ድርጅት ጉባኤ ላይ በአብዛኞቹ የአለም ሀገራት ውግዘት ማስተናገዱ ይታወሳል።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት መጠነሰፊ ድጋፍ ሲያደርግላት የነበረው የቀድሞው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር በምርጫ መሸነፍ የአሜሪካን ድጋፍ ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።
አሜሪካ ለዩክሬን ያደረገችው ድጋፍ የሚቆጫቸው የወቅቱ ፕሬዝደንት ትራምፕ ዩክሬን 500 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ብርቅ ማዕድናት ለአሜሪካ ማቅረብ አለባት ሲሉ ተደምጠዋል።
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ለማስቆም ቃል በገቡት ትራምፕ የሚመራው የአሜሪካ አስተዳደር ከሩሲያ ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል። ከሰሞኑ በአሜሪካና በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተመሩ ሁለት የልኡካን ቡድኖች ጦርነቱ በሚቆምበት ሁኔታ በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ መክሯል።
አውሮፓውያንና ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በዚህ ስብሰባ አለመሳተፋቸው ከፍተኛ ቅሬታ ውስጥ ገብተዋል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕና በዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ መካከል ያለው ክፍተት የሰፋ ሲሆን ትራምፕ ዘለንስኪን ምርጫ የማያካሄድ "አምባገነን"ሲሉ ተችተዋቸዋል።