ባይደን መካከለኛው ምስራቅን በጎበኙበት ወቅት ከአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል-ኋይት ኃውስ
የፕሬዝደንቱ ያደረጉት ጉብኝት አለም ሰላማዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳለው ኋይት ኃውስ በመግለጫው ጠቅሷል
ፕሬዝዳንት ባይደን በመካከለኛው ካገኟቸው መሪዎች ጋር ስለዩክሬን ጦርነት እና ስለ ኢራን የኑክለር መሳሪያ ጉዳይ መነጋገራቸውን ኋይት ኃውስ ገልጿል
የኋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ከአል ዐይን ነውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ያስገኘውን ውጤት ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካው ኘሬዝደንት ጆ ባይደን ከአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር በተለያዩ ቀጣናዊ አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እድል ማግኘታቸውን አድንቀዋል።
ባይደን ዉይይቱ ከአረብ ኢሬትስ ጋር ያለውን ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።የኃይት ኃውስ ቃል አቀባይ ከአል ዐይን ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ባይደን ከኢምሬትስ ፕሬዝደንት ጋር ስለነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ " ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፤በቀጣይም በኢነርጂ እና በጸጥታ ጉዳይ ያለንን ጠንካራ ትብብር እና ጥምረት እንቀጥላለን"ብለዋል።
ቃል አቀባዩ በጂዳው የጸጥታና የልማት ጉባዔ ላዮ ባደረጉት ንግግር ባይደን አሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ አጋር ሆና ትቀጥላለች ማለታቸውን ተናግረዋል።
ባለፈው በተካሄደው የጂዳው ጉባዔ ላይ የወጣው መግለጫ ተሳታፊዎች በጸጥታ ጉዳይ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመስራት ያለቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት መሪዎች ባይደን ለቀጣናው የምትሰጠውን ለአመታት የቆየ ትኩረት፣አሜሪካ ለአጋሮቿ ያላትን የጸጥታና የመከላከል ቁርጠኝነት እና መካከለኛው ምስራቅ አውሮፖን፣ አፍሪካን እና አሜሪካ በማገናኘት ያውን ሚና መረዳታቸውን በበጎ ተቀብለዋል።
ባለፈው ወር ባይደን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት አሜሪካን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።
የጆ ባይደን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ከፈረንጆቹ 2011ወዲህ እንግዳ ነገር ይዞ መጥቷል፡፡
አሜሪካ በቀጣናው ውጊያ ላይ የተሰማራ ኃይል ሳይኖራት ከፈረንጆቹ 2011 ወዲህ የአሜሪካ ፕሬዝደንት መካከለኛው ምስራቅን ሲጎበኝ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ኋይት ኃውስ ጠቅሷል፡፡
የኋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ለአል ዐይን ኒውስ እንደገለጹት አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ወቅት ካገኟቸው መሪዎች ጋር በመተባበር አሸባሪዎችን ባሉበት ቦታ ለመምታት አቅሙና እና ቁርጠኝነቱ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ የነበረው የአሜሪካ ጦር ወደ እሲያ እና ፓስፊክ ትኩረት ለማድረግ ሲባል በፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ነበር ለቆ የወጣው፡፡ በፕሬዝደንት ትራምፕ የስልጣን ዘመን ደግሞ አሜሪካ ጦሯን ከሶሪያ አስወጥታለች፡፡
የኃይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ የአሜረካው ፕሬዝደንት የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ያስገኘውን ውጤት ግልጽ አድርጓል፡፡
በቅርቡ ፕሬዝደንቱ ያደረጉት ጉብኝት አለም ሰላማዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳለው ኋይት ኃውስ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡
ኋይት ኃውስ ባይደን ባለፈው ሀምሌ ወር በሳኡዲ አረቢያ እና በእስራኤል ያደረጉት ጉብኝት የአሜሪካን እሴት ያስጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ጉብኝታቸው ተጨባጭ ውጤት ያስገኘ እና አለምን ሰላማዊ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ኃይት ኃውስ ሳኡዲ አረቢያ የአየር በረራ ከእስራኤል ወደ ሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም ከሳኡዲ አረቢያ ወደ እስራል እንዲደረግ መፍቀዷን ማስታወቋ የጉብኝቱ ወሳኝ ውጤት መሆኑን ገልጿል፡፡
የሳኡዲ አረቢያ ውሳኔ ታሪካዊ በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋትና ጸጥታ እንዲፈጠር መንገድ ይከፍታል ብለዋል ፕሬዝደንት ባይደን፡፡ ፕሬዝደንቱ ለሰባት አመታት ያህል አስከፊ የሰብኢዊ ቀውስ ውስጥ ባለችው የመን ውስጥ የነበረው ተኩስ አቁም መራዘሙ የፕሬዝደንቱ ጉብኝት ውጤት አድርገው መውሰዳቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡
ኢራንን በተመለከተ ፕሬዝደንቱ በትብብር ኢራን እንድትገለል እና ኑክለር እንዳትታጠቅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝደንት ባይደን በኢራን ጉዳይ የተናገሩት
ኢራንን በተመለከተ ፕሬዝደንቱ በትብብር ኢራን እንድትገለል እና ኑክለር እንዳትታጠቅ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ኋይት ኃውስ አስታውቋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ኢራን የኑክለር መሳሪያ እንድትታጠቅ የማስትፈቅድ ሲሆን የ”ጆይን ፕላን ኦፍ አክሽን ለማስቀጠል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ሀገራት ተጨማሪ ኑክለር እንዳያብላሉ በፈረንጆቹ 2015 የተደረሰውን ጆንት ኤንድ ኮምሬሄንሲቭ ፕላን ኦፍ አክሽን ስምምነት በኢራን ላይ ለማንቀሳቀስ ኃያላን ሀገራት ለወራት እንቅስቃሴ እያካሄዱ ነው፡፡ አሜሪካ ከስምምነቱ በፈረንጆቹ በ2018 ወጥታለች፡፡
ስምምነቱ ኢራን ኑክለር እንዳታብላላ እግድ የሚጥል ሲሆን የቀጣናው ሀገራት ይህ ተግባራዊ ስለመሆኑ ዋስትና የላቸውም፡፡
ኢራን ስምምነቱን ተግባራዊ ለማደረግ በምእራባውያን የተጣለው ማእቀብ መነሳትን እንደቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች ተብሏል፡፡
የምግብ እና የአየር ንብረት ቀውስ
በዚሁ መግለጫ ወራትን ባስቆጠረው በሩሲያ እና ዩክሬን ምክንያት የተፈጠረውን የምግብ ቀውስ ለመፍታት የገልፍ ትብብር ም/ቤት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጭ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በምርት መቀነስና በዋጋ መጨመር ምክያት እየዋዠቀ ያለውን የነዳጅ ገበያ በተመለከተ ሳኡዲ አረቢያ የአለምአቀፉን የነዳጅ ገበያ በማስተካከል ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲኖር ትሰራለች ብሏል መግለጫው፡፡
አሜሪካ የነዳጅ አምራች ሀገራት የነዳጅ ምርትን በ50 በመቶ ለመጨመር መስማማታቸውን ፕሬዝደንት ባይደን ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዝንቱ ባይደን እንደገለጹጽ የተወሰዱት እና እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ገበያውን ያረጋጋሉ፡፡