ብሊንከን ዋሽንግተን ኢራን ለሩሲያ ባለስቲክ ሚሳይል አሳልፋ እንዳትሰጥ በግሏ አስጠንቅቃታለች ብለዋል
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ ከኢራን የባለስቲክ ሚሳይሎች መቀበሏን እና በሳምንታት ውስጥ በዩክሬን ጦርነት ልትጠቀምባቸው እንደምትችል ተናገሩ።
ሚኒስትሩ የቴህራን እና የሞስኮ ትብብር የአውሮፓን ደህንነት ስጋት ላይ ጥሎታል ብለዋል።
ብሊንከን በኪቭ ሊያደጉት ካሰቡት ጉብኝት ቀደም ብለው በለንደን በተካሄደ ስብሰባ ላይ ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ጸሀፊ ዴቪድ ላሚ ጎን ሆነው ባሰሙት ንግግር ዋሽንግተን ኢራን ለሩሲያ ባለስቲክ ሚሳይል አሳልፋ እንዳትሰጥ በግሏ አስጠንቅቃታለች።
ሚኒስትሩ እንዳሉት ከሆነ ኢራን የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ የማትቀበል ከሆነ ተጨማሪ ማዕቀብ ይጣልባታል።
የደህንነት ምንጮችን ጠቅሰው "ሩሲያ እነዚህን የባለስቲክ ሚሳይሎች እየተቀበለች መሆኗን እና በሳምንታት ውስጥ በዩክሬኑ ጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ ልታውላቸው ትችላለች" ሲሉ የተናገሩት ብሊንከን አሜሪካ ይህን መረጃ በመላው አለም ላሉ አጋሮቿ አጋርታለች ብለዋል።
ሩሲያ የኢራን ሚሳይሎችን ማግኘቷ ያሏትን የጦር መሳሪያዎች ከግባር በረጅም ርቀት ላይ ያሉ ኢላማዎችን ለመምታት እንድትጠቀም ያስችላታል ብለዋል ብሊንከን።
"ይህ ክስተት እና በሩሲያ እና በኢራን መካከል ያለው ትብብር እያደገ መምጣት የአውሮፓን ደህንነት ስጋት ላይ እንደሚጥል እና የኢራን ትርምስ የመፍጠር ተጽዕኖ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደሚሻገር ያሳያል።"
ብሊንከን አክለው እንደገለጹት ሩሲያ ለኢራን በኑክሌር ጉዳዮች ጨምሮ ቴክኖሎጂዋን ለኢራን ስታጋራ ነበር። አሜሪካ በኢራን ላይ የምትጥለው ተጨማሪ ማዕቀብ የኢራን ኤየርን እንደሚያካትት እና ሌሎች ሀገራትም አዲስ ማዕቀብ ያሳውቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሊንከን ተናግረዋል።
ኢራን ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እያስታጠቀች ስለሚለው ሪፖረት በቅርቡ የተጠየቁት የሩሲያ መንግስት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ቤስኮፕ "ኢራን አጋራችን ነች"፣ ነገርግን እንዲህ አይነት ሪፖርቶች ትክክል አይደሉም የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረችበት ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ወዲህ ቴህራን አመት እና ሞስኮ ግንኙነታቸውን አጠናክረዋል።