ቦሪስ ጆንሰን በጠበበ ልዩነት የፓርያቸውን የድጋፍ ድምጽ በማግኘታቸው ነው ከስልጣን ከመወገድ የተረፉት
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከስልጣን ከመወገድ ተረፉ፡፡
ጆንሰን ህግ አለማክበራቸው አላስተማመነንም ባሉ የፓርቲያቸው የመሪው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ህግ አውጭ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ ከተሰጠ የመተማመኛ ድምጽ ነው የተረፉት፡፡
ከ359ኙ የፓርቲው ህግ አውጪ አባላት የ211ዱን የድጋፍ ድምጽ ማግኘታቸው በጠባብ ልዩነትም ቢሆን በስልጣን ላይ ሊቆዩ የሚችሉበትን እድል አስገኝቶላቸዋል፡፡
ጥንታዊ ቅርሶችን ይዞ የተገኘው ብሪታኒያዊ በኢራቅ 15 ዓመት ተፈረደበት
ወግ አጥባቂው ፓርቲ ትናንት ሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይቀጥሉ አይቀጥሉ በሚለው ላይ የመተማመኛ ድምጽ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ሆኖም በጠባብ ልዩነት የተገኘ ነው የተባለለት የድጋፍ ድምጹ ጆንሰን አሁንም ለጊዜው እፎይ ቢሉም ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ማሳያ ነውም ተብሏል፡፡
ጆንሰን ሁኔታውን ተከትሎ ከስካይ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ያገኙት ድምጽ "ወሳኝ" ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የ41 በመቶው ያህሉን የፓርቲ ጓዶቻቸውን ድጋፍ አጥተው ይህን ማለታቸው ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡
ብሪታኒያን ከአውሮፓ ህብረት አባልነት የማስወጣቱን ሂደት ከዳር ያደረሱት ጆንሰን ከምግብና ነዳጅ ውድነቶች ጋር በተያያዘ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጫና ውስጥ ገብተዋል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተጣሉ እገዳዎችን በመተላለፍ ጆንሰንና ሌሎች የመንግስታቸው ባለስልጣናት በቤተ መንግስት የመዝናኛ ዝግጅቶች መጠመዳቸው ከባድ ቁጣን ቀስቅሶ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ከቷቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡