ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃምሌ ላይ እንደሚለቁ መናገራቸው ይታወሳል
ባለፈው ወር ከጠቅላይ ሚኒስትርነትና ከፓርቲ መሪነት መልቀቃቸውን ያሰውታወቁት ቦሪስ ጆንሰን በግሪክ መታየታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ቢገልጹም አሁንም የሀገሪቱ መንግስት መሪ ናቸው፡፡
ይሁንና አሁን ብሪታኒያን ለቀው ለግብይት ግሪክ መታየታቸው በርካቶችን አነጋግሯል፡፡
ቦሪስ ጆንሰን እና ባለቤታቸው በአንድ የግሪክ ሱፐር ማርኬት ውስጥ የዕቃ መሸመቻ ቅርጫት ይዘው መታየታቸውን የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣኑን ቢለቁም፤ ለብሪታኒያ የሚሆን መሪ እስኪመረጥ ድረስ መሪ መሆናቸው እየዘነጉት ነው የሚሉ ትችቶች ደርሰዋቸዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገራቸው ችግር ላይ ሆና ለሸመታ ወደ ሌላ ሀገር መሄዳቸው ትክክል አይደለምም እያስባላቸው ነው፡፡
ቦሪስ ጆንሰን እስከ ፈረንጆቹ መስከረም አምስት ቀን 2022 ድረስ በስልጣን ይቆያሉ፡፡ ቦሪስ ጆንሰን እና ባለቤታቸው በግሪክ ሱፐር ማርኬት ውስጥ ዕቃ ሲገዙ ብዙ ሰዎች ያወቋቸው ሁሉ አይመስሉም ነበር ተብሏል፡፡
ስልጣን እንደሚለቁ ያሳወቁት ቦሪስ ጆንሰን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ዩክሬን ሊጓዙ እንዳቀዱ ቀደም ብለው ማሳወቃቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ “ኃላፊነት ተሰምቷቸው ነው” በሚል ሲገለጽ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ስልጣናቸውን ለተተኪያቸው እንደሚያስረክቡ ሃምሌ ወር ላይ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ጆንሰን ስልጣን እንደሚለቁ የገለጹት፤ ቁልፍ የስልጣን አጋሮቻቸውን በማጣታቸው ነው ተብሏል፡፡
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በርካታ ዕጩዎች ቀደም ሲል የቀረቡ ቢሆንም አሁን ግን ሶስት ዕጩወፐች ብቻ ቀርተዋል፡፡