ተመድ በዩክሬን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ ከጦር ነጻ ቀጠና እንዲቋቋም ጠይቋል
ዩክሬን እና ሩሲያ እርስበእርሳቸው የኑክሌር ጣቢያውን በማጥቃት እየተካሰሱ ነው
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ፋብሪካውን ወደ ዩክሬን እንድትመልስ ጠይቀዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በዩክሬን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ አካባቢ የደረሰው ጥቃት በአካባቢ ከጦር ነጻ ቀጣና ይኑር የሚል ጥሪ ለማድረግ እንዳስገደደው አስታውቋል፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን ከአውሮፓ ትልቅ የሆነውን እና በዩክሬን የሚገኘውን የኑክሊየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጥቃት በማድረስ እርስ በእርሳቸው በመካሰስ ላይ ባሉበት ወቅት ተመድ ተመድ ከጦር ነጻ ቀጣና እንዲቋቋም ሀሳብ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በደቡባዊ ዩክሬን የሚገኘው እና ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” እንደጀመረች በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር የዋለው የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጥቃት ድርሶበታል ተብሏል፡፡
የዩክሬኑ ኢነርጋቶም ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የዛፖሪዝሂያ ህንጻ ሬዲዮ አክቲቭ መሳሪያዎች ያሉበትን ቦታ ጨምሮ አስምት ቦታዎች ላይ ጥቃት ደርሶበታል ብሏል፡፡ ነገርግን በሩሲያ የተሾሙት ባለስልጣናት ዩክሬን ፍብሪካውን ማጥቃቷን እና ስራ ማስተጓጎሏን መገለጻቸውን ሮይተርስ የሩሲያውን ታስ የዜና አገልግሎት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ሁኔታውን ለመገምገም በትናንትናው እለት የተሰበሰው ተመድ፣ ሁለቱም አካላት በፍብሪካው አካባቢ ውጊያ እንዲያቆሙ ጠይቋል፡፡
“ተቋሙ እንደ ወታደራዊ ዘመቻ አካል መሆን የለበትም። ይልቁንም የአከባቢውን ደህንነት ለማረጋገጥ ከወታደራዊ አንቅስቃሴ ነጻ ማድረግ ዙሪያ አስቸኳይ የቴክኒካል ደረጃ ስምምነት ያስፈልጋል” ሲል ጉቴሬዝ በመግለጫው ተናግሯል።
ዛፖሪዝሂያ የኑውክሌር ኃይል ጣቢያ በሩሲያ የተያዘ ሲሆን በዩክሬን ባለሙያዎች እየተዳደረ ይገኛል፡፡
በተመድ ስብሰባ ላይ አሜሪካ ቦታው ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆንና ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ቦታውን እንዲጎበኝ አሳስባለች፡፡
የሩስያ የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ እንዳሉት አለም "ከቼርኖቤል ጋር ሊወዳደር የሚችል የኒውክሌር አደጋ አፋፍ ላይ እየተገፋች ነው" ብለዋል። በዚህ ወር የየአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ባለስልጣናት ቦታውን ሊጎበኙ እንደሚችሉም ተናግረዋል።
ሮይተርስ በፋብሪካው ውስጥ ስላለው ሁኔታ ከሁለቱም ወገኖች የሚመጡ ሪፖርቶችን በራሱ ማረጋገጥ አለመቻሉን ገልጿል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ፋብሪካውን ወደ ዩክሬን እንድትመልስ ጠይቀዋል።