የብሪታንያ ሙዚየም የተሰረቁበትን 2ሺ እቃዎች እየፈለገ ነው
ሙዚየሙ የትኞቹ ቁሶች እንደተሰረቁ ለማወቅ የፎረንዚ ምርመራ እያደረገ ነው ተብሏል
ባለፈው ሳምነት ለእቃዎች መመዝበር ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሰራተኞች ተባረዋል
የብሪታንያ ሙዚየም ወርቅና እንቁዎችን ጨምሮ በረጅም የጊዜ ሂደት የተለያዩ እቃዎች መሰረቁን አስታውቋል።
ሆኖም እቃዎችን የማስመለስ ጥረቶች ዝቅተኛ መሆናቸውን ሙዚየሙ ተናግሯል።
ከለንደን በብዛት ከሚጎበኙ መዳረሻዎች አንዱ የሆነው ብሪታንያ ሙዚየሙ፤ ባለፈው ሳምንት ለእቃዎች መመዝበር ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን ሰራተኞቹን አሰናብቷል።
የሙዚየሙ ዳይሬክተር ሀርትዊግ ፊሸር በስርቆቱ ላይ ምርመራ ለማድረግ ክፍተት በማሳየታቸው ስራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል።
የቀድሞ የእንግሊዝ የገንዘብ ሚንስትር የሆኑት የሙዚየሙ የቦርድ ሰብሳቢ ኦዝቦርን፤ ድርጊቱን መቶ ዓመታትን በተሻገረ ተቋም መከሰቱ እንግዳ አይደለም ብለዋል።
እስካሁን የትኞቹ ቁሶች እንደተሰረቁ ለማወቅ የፎረንሲክ ምርመራ እየተደገ ነው ተብሏል።
በግምት እቃዎቹ ሁለት ሽህ እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።
ስርቆቱ በሙዚየሙ ሰራተኞች ተፈጽሞ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳለም ሰብሳቢው ተናግረዋል።