ፕሬዝዳንት ፑቲን ከቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ እንዲታገዱ የብሪታኒያ እጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠየቁ
ፕሬዝዳንቱ ከጉባኤው እንዲታገዱ ጥያቄ ያቀረቡት የብሪታንያ እጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ናቸው
የዘንድሮው ቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ የፊታችን ህዳር በኢንዶኔዥያ ያካሄዳል
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ እንዲታገዱ የብሪታኒያ እጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠየቁ።
በኢኮኖሚ መጠናቸው ከእንደኛ እስከ 20 ባሉ ሀገራት የተመሰረተው የቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ በቀጣዩ ህዳር ወር ላይ በኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የዚህ ቡድን አባል ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት መግቧን ተከትሎ በዚህ ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ አሜሪካ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ፍላጎት እንዳላቸው ከዚህ በፊት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ብሪታንያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለምራት በእጩነት የቀረቡት ሪሺ ሱናክ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዚህ ጉባኤ ላይ እንዳይሳተፉ እገዳ ሊተላለፍባቸው እንደሚገባ መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ በዩክሬናዊያን ላይ ያን ሁሉ በደል እያደረሰች ከዓለም መሪዎች ጎን በጉባኤው ላይ ልትካፈል አይገባም የሚሉት እጬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጦርነቱን ካላቆመ በጉባኤው ላይ መሳተፍ እንደሌለበት ተገልጿል፡፡
አሜሪከንን ጨምሮ ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ፕሬዝዳንት ፑቲን በቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንዳይሳተፉ ቢፈልጉም አንድን ሀገር ከቡድኑ እንዲባረር ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው ህንድ፣ ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች ሀገራት የግድ መስማማት አለባቸው ተብሏል።
ሩሲያ ከስምንት ዓመት በፊት ክሪሚያን ወደ ግዛቷ መጠቅለሏን ተከትሎ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን ፣ሩሲያ እና ጣልያን አባል ከሆኑበት የቡድን ስምንት አባል ሀገራት ጉባኤ ውሰጥ መባረሯ ይታወሳል።
የአሜሪካ ፕሬዘዳንት የደህንነት አማካሪ ጃክ ሱልቪያን በጉዳዩ ላይ እንደተናገሩት በቡድን 20 ላይ ሩሲያ አባል ሆና ከቀጠለች ጉባኤው የማይጠቅም ይሆናል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ሩሲያ በዓለም አቀፍ ተቋማት እና ጉባኤዎች ላይ እንደከዚህ ቀደሙ አይሆንላትም ያሉት አማካሪው ከቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ልትሳተፍ አትችልም ሲሉም አክለዋል።
ከዩክሬን ጋር በገባችበት ጦርነት ምክንያት ማዕቀቦችን እያስተናገደች የምትገኘው ሩሲያ በበኩሏ ከቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ ማንም ሊያባርረኝ አይችልም ብላለች።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም በዚህ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ በይፋ የተናገሩ ሲሆን ይህ ጉባኤ ምን ሊመስል እንደሚችል ከወዲሁ ትኩረቶችን ስቧል፡፡
በአውሮፓ በተከሰቱ የመብረቅ አደጋዎች የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
በማዕከላዊ እና ደቡባዊ የአውሮፓ ሀገራት በደረሱ የመብረቅ አደጋዎች ከሞቱት 12 ሰዎች ውስጥ ሶስቱ ህጻናት እንደሆኑም ተገልጿል።