5 ሺህ የሚሆኑ የብሪታንያ ባቡር ትራንስፖርት ሰራተኞች ስራ አቁመዋል
የእንግሊዝ ባቡር ትራንስፖርት ካፒቴኖች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተነግሯል።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ የዓለም ምግብና ነዳጅ ዋጋ በማሻቀብ ላይ ይገኛል።
የዋጋ ግሽበትን ተከትሎም በርካታ ሀገራት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው።
ሩሲያ 40 በመቶ የአውሮፓ ሀገራትን ነዳጅ ፍላጎት የምትሸፍን ቢሆንም ምዕራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ማዕቀቦችን በመጣል ላይ ናቸው።
በዚህና ሌሎች ምክንያቶች በአውሮፓ የምርቶች ዋጋ እና አቅርቦት ፍላጎት በመጨመሩ ዜጎች መንግስቶቻቸው የተለያዩ የኢኮኖሚ ማረጋጊያ እርምጃዎች እንዲወስዱላቸው በመጠየቅ ላይ ናቸው።
ሩብ በመቶ ያህሉ የብሪታንያ ባቡር ትራንስፖርት ሾፌሮች የ24 ሰዓታት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
አሽከርካሪዎቹ የስራ ማቆም አድማ የምርት መንግስት ለኑሮ ውድነቱ ምላሽ ይስጥ እና የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን በሚል ነው።
ተጨማሪ የባቡር ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የፊታችን ረቡዕ የስራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ የሰራተኞቹ ማህበር አስጠንቅቋል።
ባሳለፍነው ሳምንት የዓለማችን ግዙፍ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የጀርመኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ ሰራተኞች የአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ይታወሳል።
ሰራተኞቹ ድንገቴ ሳይሆን የታቀደ አድማ የመቱት ኩባንያው የተጠየቀውን የደመወዝ ማስተካከያ እንዲያደርግ ቢጠየቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንደነበር በወቅቱ ተገልጿል።
አድማውን ተከትሎም የሉፍታንዛ አየር መንገድ ከአንድ ሺህ በላይ በረራዎቹን ለመሰረዝ ተገዷል ተብሏል።
በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች ባሉ አውሮፕላን ጣቢያዎች ያሉ ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አስቀድመው አድማ እንደሚመቱ አስጠንቅቀው ነበርም ተብሏል።