ብሪታኒያ፤ የ”ሩሲያ ተጨማሪ ወታደሮችን እመለምላለሁ ማለት” ግልጽ አይደለም አለች
የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር፤ “የሩሲያ የወታደሮች ቁጥር መጨመር በዩክሬን ጦርነት ትልቅ ተጽዕኖ አይኖረው”ም ብሏል
ሞስኮ በኪቭ ላይ በማካሄድ ላይ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተቃወሙት ሀገራት ብሪታኒያ አንዷ ነች
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የዩክሬን ጦርነት ሰባተኛ ወሩን በያዘበት ወቅት የሩስያ ጦር ኃይል ከነበረበት 1ነጥብ 9 ሚሊዮን ወደ 2ነጥብ 04 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዳቸውን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በውሳኔው ግራ የተጋባቸው ብሪታኒያ፤ የ”ሩሲያ ተጨማሪ ወታደሮችን እመለምላለሁ ማለት” ግልጽ አይደለም ማለቷ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ፤ሩሲያ ተጨማሪ ወታደሮችን እመለምላለሁ ማለቷንና እንዴት እንደምታገኝ ግልጽ ነው ብሏል፡፡
“ሩሲያ የወታደሮቿን ቁጥር ማሳደግ የፈለገቸውን ብዙ በጎ ፈቃደኞችን በመመልመል ወይስ የግዳጅ ምልመላ በማሳደግ ?” የሚል ጥያቄም አቅርቧል ሚኒሰቴሩ በትዊተር ገጹ ባጋራው ጽሁፉ፡፡
ያም ሆኖ ሩሲያ የወታደር ቁጥሯ ስለጨመረች በዩክሬን የምታደርገው የውጊያ ኃይሏ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል ወይም በጦርነቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖሯል ማለት አይደለም ብሏል፡፡
"ሩሲያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አጥታለች፣ በጣም ጥቂት አዳዲስ የኮንትራት ሰራተኞች እየተመለመሉ ነው እንሱም ቢሆኑ ከሩሲያ ግዛት ውጭ ለማገልገል አይገደዱም" ብሏል የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር፡፡
ብሪታኒያ ፤ የክሬምሊን ሰዎች በኪቭ ላይ እያካሄዱት ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተቃወሙት ሀገራት መሆኗ ይታወቃል፡፡
ተሰናባቹ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ፤ ሁለት ጊዜ በኪቭ ያደረጉት ጉብኝትና የሰጡት የአጋርነት ማረጋገጫ የዚሁ ማሳያ እንደሆነ ይነገራል፡፡
በዚህም ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰንን የሞስኮ ባለስልጣናት ክፉኛ እንደተቀየሟቸው ይታወቃል፡፡