እንግሊዛውቷ ታዳጊ “የጠፋችው ድመት” በሚል ርዕስ ነው መጽሃፍ ያሳተመችው
እንግሊዛውቷ የ5 ዓመት ታዳጊ በራሷ አዘጋጅታ በሳተመችው አዲስ መጽሃፍ አየዲስ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ባለቤት ለመሆን በቅታለች።
ቤላ ጄይ የተባለችው ታዳጊዋ በልጅነት እድሜዋ መጽፋ በማሳተም እና በተቋሙ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ 1000 ቅጂ በመሸጥ የአዲስ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት መሆኗን ነው የዓለም የድነቃ ድንቆቸ መዝገብ (ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ) ያረጋገጠወ።
ቤላ ጄይ “የጠፋችው ድመት” የሚለወ መጽሃፏን ስታዘጋጅ በእናቷ ቼልሲ ሳይም መጠነኛ እገዛ እንዳገኘች የተነገረ ሲሆን፤ መጽሃፉንም ጂንጀር ፋየር ፕሬስ እንዳሳተመው ተነግሯል።
የቤላ እናት ቸልሲ ስለ ልጇ ስትናገር “ሁለታችንም ማለትም እናት እና አባቷ በልጃችን ተግባር በጣም ኮርተናል” ብላች።
“መጽሃፉ ብቻዋን ከቤት ወጥታ ስለጠፋች እና ከጠፋች በኋላ እናቷ ሳተውኖር መውጣት እንዳልነበረባት ስለተረዳች ድመት ነው የሚተርከው” ያለችው እናት ቸልሲ፤ ህጻናት ብቻውን መውጣት እንደሌለባቸው የሚያስተምር ነው ብላለች።
ልጇ ቤላ መጽሃፉ ላይ ያሉ ሁሉንም ስእሎች በራሷ እንደሳለቻቸው በመግለጽ፤ አሁን ላይ የተሰጣት እውቅና በጠፋችው ድመት መጽሃፍ ላይ ለሰራችው ጠንካራ ስራ የተከፈላት ዋጋ ነው ብላለች።
ቤላ ጄይ መጽሃፍ የመጻፍ ስራዋን እንደምትቀጥል እና በቅረቡም “የጠፋቸውም ድምት 2” ይዛ እንደምትመጣ እናቷ ቸልሲ አስታውቃለች።