ብሪታንያ የባህር ሀይል ጦሯን ለማዘመን 5 ቢሊዮን ዶላር መደበች
የአውሮፓ ሀገራት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ለጦር መሳሪያ ሸመታ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ላይ ናቸው
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በአውሮፓ ውጥረት አንግሷል
ብሪታንያ የባህር ሀይል ጦሯን ለማዘመን 5 ቢሊዮን ዶላር መደበች።
19ኛ ወሩ ላይ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አውሮፓ ከ70 ዓመት በኋላ ከባድ ጦርነት እንድታስተናግድ አድርጓታል።
ይህን ተከትሎም በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ለጦር መሳሪያ የሚመድቡት ዓመታዊ በጀት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
ብሪታንያ የባህር ሀይሏን ለማዘመን በሚል 5 ቢሊዮን ዶላር መመደቧን አስታውቃለች።
ሀገሪቱ ይህን ከፍተኛ በጀት ለመከላከያ ስታውል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
ምዕራባዊያን ሀገራት በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ትተውት ወደ ነበረው የኒክሌር አረር ፉክክር መመለሳቸውም ተገልጿል።
ሩሲያ የዘመናዊ እና ጠንካራ የኒዩክሌር አረር ባለቤት ሀገር ስትሆን ብሪታንያ ሞስኮን ለመገዳደር አዲስ እቅድ አውጥታ በመስራት ላይ መሆኗን አስታውቃለች።
የብሪታንያ መከላከያ ሚንስትር ግራንት ሼፕስ የባህር ላይ ጥቃቶችን ማድረስ የሚያስችል ኒዩክሌር ተሸካሚ መርከቦችን እንሰራለን ብለዋል።
ሚንስትሩ አክለውም ብሪታኒያ በታሪኳ ታጥቃው የማታውቀው የባህር ላይ ጥቃት ማቀላጠፊያ መርከብ ትታጠቃለች ነው ያሉት።
ከብሪታንያ በተጨማሪ ጀርመንም የመከላከያ በጀቷን ያሳደገች ሌላኛዋ የአውሮፓ ሀገር ስትሆን በተለይም ብዙ ኪሳራዎችን ካደረሰባት ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ወታደራዊ በጀቷን ከፍ ማድረጓ ነው የተነገረው።