ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦር ከተማዘዘች ወዲህ ጄቶቿ ከምዕራባውያኑ የጦር አውሮፕላኖች ጋር በተደጋጋሚ ተፋጠዋል
ሩሲያ በጥቁር ባህር በኩል ወደ ድንበሯ የተቃረቡ ሁለት የብሪታንያ ጄቶችን እንደመለሰች አስታውቃለች።
ሞስኮ ሁለት ተዋጊ ጄቶችን ልካ የብሪታንያን ጄቶች መመለሷን ያሳያል ያለችውን የቪዲዮ ምስልም ለቃለች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ “የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች ሲጠጓቸው (የብሪታንያ ጄቶችን) በፍጥነት ዞረው ወደመጡበት ተመልሰዋል” ብሏል።
ብሪታንያ ግን እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ጦር ከተማዘዘች ወዲህ ጄቶቿ ከምዕራባውያኑ የጦር አውሮፕላኖች ጋር በተደጋጋሚ ተፋጠዋል።
የአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ፖላንድ የጦር አውሮፕላኖች በጥቁርና ባልቲክ ባህር ሲበሩም ጄቶቿን ልካ ከአካባቢው እንዲወጡ ማድረጓ ይታወሳል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic