55 በመቶ የሚሆኑት የብሪታንያ ዜጎች በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ለመቀጠል ድምጽ እንደሚሰጡ ተናገሩ
ብሪታንያዊያን ብሬግዚት የተሳሳተ ምርጫ ነው አሉ።
ብሬግዚት ስህተት ነበር የሚሉት ብሪታንያውያን በዚህ ወር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል ተብሏል።
ዩጎቭ ሰርቬይ የተባለ ተቋም ባካሄደው ጥናት ነው ከግማሽ የሚልቁ ብሪታንያዊያን ሀገራቸው ከአውሮፓ ህብረት መነጠሏን የተቃወሙት።
የምጣኔ ሀብት ጠቀሜታዎችን ለማግኘት እ.አ.አ ሰኔ 2016 የአውሮፓ ህብረትን ለመልቀቅ የተደረገው ምርጫ፤ 57 በመቶ ብሪታንያውያን ውሳኔ የተሳሳተ ነው ብለዋል።
32 በመቶዎቹ ደግሞ ትክክል ነው ብለዋል።
ከግማሽ በላይ (55 በመቶ) የሚሆኑት በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ለመቀጠል ድምጽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
31 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህዝበ ውሳኔው እንደገና ቢካሄድ መነጠልን እንመርጣለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ በግንቦት ወር ላይ ብሬግዚት ጥቅማ ጥቅሞችን እያስገኘ ነው ብለዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የታክስ እና የጉምሩክ እፎይታዎችን እና ቀላል የንግድ ደንቦችን የያዙ ልዩ ዞኖች የብሪታንያ ምጣኔ ሀብት አያሳድጉም ይላሉ። ነገር ለክልላዊ ልማት ውስን ሚና ሊኖራቸው ይችላል ባይ ናቸው።
ሮይተርስ እንደዘገበው እንደ ሌሎች ግዙፍ ምጣኔ ሀብቶች የብሪታንያ ንግድና ኢንቨስትመንት ከ2016 አጋማሽ ጀምሮ እምብዛም አላደገም።
ከሁለት ሽህ በላይ የብሪታንያ ህዝብ ላይ በተደረገው ጥናት፤ 63 በመቶ የሚሆኑት ብሬግዚን ከስኬት የበለጠ እንደ ውድቀት ቆጥረዋል። ከ12 በመቶ በላይ የሚሆኑት ብቻ እንደ ስኬት ይቆጥሩታል።