ለመስረቅ በገባባቸው ቤቶች ምግብ የሚሰራው እና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳው ሌባ
ግለሰቡ ለመስረቅ በገባባቸው ቤቶች ያልተሰቡ ነገሮችን በማድረግ ታዋቂ ሆኗል
ምግብ ከመስራት ጀምሮ የተዘበራረቁ እቃዎችን መልክ መልክ አስይዞ የወጣው ይህ ሌባ በመጨረሻም ከእስር አላመለጠም
ለመስረቅ በገባባቸው ቤቶች ምግብ የሚሰራው እና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳው ሌባ
ትውልደ ፖላንዳዊው ዳሚያን ዎጅኒሎዊች በእንግሊዝየሚኖር እንግሊዛዊ ሲሆን በማያውቀው ቤት ውስጥ በመግባት ስርቆት በመፈጸም ይታወቃል፡፡
ይህ እንግሊዛዊ እንደተለመደው ንብረቶችን ለመስረቅ በገባባቸው ሁለት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ያልታሰቡ ነገሮችን አድርጎ ተሰውሯል፡፡
ባለቤቶቹ በቤት ውስጥ እንደሌሉ አስቦ የገባው ይህ እንግሊዛዊ ለባለንብረቶቹ ምግብ አብስሎ፣ የሚጠጣ ወይን አዘጋጅቶ፣ የቆሸሹ ልብሶችን አጥቦ ሲያስተካክል በድብቅ በተገጠመው የመኖሪያ ቤቱ ካሜራ ላይ ታይቷል፡፡
ግለሰቡ ከዚህ በተጨማሪም የጓሮ አትክልቶችን ሲኮተኩት፣ ቆሻሻ ሲጸዳ እና ወደ ማጠራቀሚያ ቦታዎች ሲወስድም ታይቷል፡፡
እንዲሁም ለባለቤቶቹ በተወው ማስታወሻ መልካም ማዕድ መመኘቱን እና እንዲዝናኑም በእጁ የተጻፈ ጽሁፍም አስቀምጧልም ተብሏል፡፡
ከአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በፊት የእንግሊዝን አሸናፊነት የሚገልጽ ንቅሳት የተነቀሰው እንግሊዛዊ
መኖሪያ ቤቷ በማታውቀወ ሰው ተውቦ እና ተስተካክሎ የሚጠብቃት አንድ ነዋሪ በበኩሏ የሚውቀኝ አንድ ሰው እየረዳኝ እንደሆነ እያሰብኩኝ ነበር ስትል ተናግራለች፡፡
ግለሰቡ ለጉብኝት ወደ ሌላ ሀገር በሄዱ እና በካርዲፍ በሚኖሩ ሌላ መኖሪያ ቤት ለስርቆት ከገባ በኋላ ምግብ አቅርቦ በመመገብ ላይ እያለ በስልካቸው ላይ በገጠሙት የደህንነት ካሜራ አማካኝነት ካዩ በኋላ ለፖሊስ ጠቁመዋል፡፡
ፖሊስም ወዲውኑ ይህንን ሌባ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን የ22 ወራት እስር ፈርዶበታል ሲል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡