ቡርኪናፋሶ ወታደራዊ አስተዳድሯን ለአምስት ዓመት አራዘመች
ሀገሪቱ ከምርጫ በፊት ሽብርተኞችን መደምሰስ እንዳለባት የሀገሪቱ የሽግግር ፕሬዝዳንት ተናግረዋል
ካፒቴን ትራውሬ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ሲቆጣጠሩ በሁለት ዓመት ውስጥ ምርጫ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር
ቡርኪናፋሶ ወታደራዊ አስተዳድሯን ለአምስት ዓመት አራዘመች፡፡
ኮለኔል ሄነሪ ዳሚባ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬ ላይ በፈጸሙት መፈንቅለ መንግስት ነበር ስልጣን የተቆጣጠሩት፡፡
ኮለኔል ሄነሪ በወቅቱ መፈንቅለ መንግስት ለመፈጸም ያነሳሳቸው የሀገሪቱ መንግስት ሽብርተኞችን ማጥፋት አልቻሉም በሚል ነበር፡፡
ይሁንና ካፒቴን ኢብራሂም ትራውሬ በሀይል የመንግስትን ስልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ አስተዳድር መፍትሔ አላመጣም በሚል ነበር ሌላ መፈንቅለ መንግስት የተፈጸመው፡፡
ላለፉት ሁለት ዓመታት ስልጣን የተቆጣጠረው የካፒቴን ትራውሬ ወታደራዊ መንግስት በ21 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ በማድረግ ስልጣን በህዝብ ለተመረጠ አካል ስልጣን እንደሚያስረክብ ቃል ገብቶም ነበር፡፡
ካፒቴን ትራውሬ በቡርኪናፋሶ አሁንም ሽብርተኞች እንዳልተደመሰሱ ምርጫ ከመካሄዱ በፊትም የሀገሬውን ህዝብ እየገደሉ ያሉትን ሽብርተኞች ማጥፋት ያስፈልጋል በሚል የምርጫ ጊዜውን አራዝመዋል፡፡
አሁን ስልጣን የተቆጣጠረው አካል ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ስልጣኑን ይዞ እንደሚቀጥል የሀገሪቱ የሽግግር ወታደራዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ትራውሬ ተናግረዋል፡፡
ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ
እንደ ኤኤፍፒ ዘገባ ከሆነ ምርጫ ለቡርኪናዊያን ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም ያሉ ሲሆን የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሽብርተኞችን ማጥፋት ነው ብለዋል፡፡
ቡርኪናፋሶን ጨምሮ ኒጀር እና ማሊ ስልጣን በሀይል መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ከአፍሪካ ህብረት እና ከምዕራብ አፍሪካ አባልነት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ወይም ኢኮዋስ መታገዳቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህ ሀገራት በምላሻቸውም ኢኮዋስ በምዕራባዊያን ሀገራት ተጽዕኖ ስር ወድቋል በሚል ራሳቸውን ከአባልነት ማገዳቸውን አስታውቀዋል፡፡