ወታደሮቹ የተላኩት የሀገሪቱን መሪ ኢብራሂም ትራኦሬን እና የቡርኪናፋሶ ህዝብ ደህንነት ለማረጋገጥ"100 የሩሲያ ወታደሮች መላካቸውን ገልጿል
ሩሲያ ወታደሮች ወደ ቡርኪናፋሶ መላኳ ተገለጸ።
የሩሲያ ወታደሮች ወደ ቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ኡጋድጉ ባለፈው ረብዕ እለት መላካቸውን ሮይተርስ ሁለት የውጭ የጸጥታ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ምዕራብ አፍሪካ ስትልክ ይህ የመጀመሪያዋ ነው ተብሏል።
ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሰት ባደረጉ ወታደሮች የምትመራው ሀገሪቱ በ2023 የፈረንሳይ ወታደሮችን ካስወጣች ጀምሮ ከሞስኮ ጋር ያላት ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ይህ ግንኙነት፣ቡርኪናፋሶ የዋግነር ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱባት ጎረቤቷ ማሊ ከሩሲያ ጋር በጸጥታ ጉዳይ የሚኖራትን ትብብር ታጠናክራለች የሚል ጥርጣሬ እንዲጨምር አድርጓል።
ለሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቅርበት እንዳለው የገለጸው አፍሪካን ኮርፕስ በቴሌግራም ገጹ ላይ "የሀገሪቱን መሪ ኢብራሂም ትራኦሬን እና የቡርኪናፋሶ ህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ"100 የሩሲያ ወታደሮች መላካቸውን ገልጿል።
አፍሪካ ኮርፕስ አክሎም ተጨማሪ 200 ወታደሮች በቅርቡ ይላካሉ ብሏል።
ሌላው ለክሬሚሊን ቅርበት ያለው የአፍሪካ ጉዳዮችን የሚዘግበው አፍሪካ ኢኒሼቲቭ በቴሌግራም ገጹ ወታራዊ መለዮ የለበሱ ሰዎች ከአውሮፕላን ላይ እቃ ሲያወርዱ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል።