በቡርኪናፋሶ ዳኞች በግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ተመለመሉ
"የዳኞች ማህበራት እነዚህ ዳኞች በቅርቡ የአሁኑ መንግስት ዋነኛ ደጋፊ ነን የሚሉ ሰዎች ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥተው ነበር" ብለዋል ማህበራቱ።
በቡርኪናፋሶ ቢያንስ ስድሰት ዳኞች ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ መመልመላቸውን ሶስት የዳኞች ማህበራት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል
በቡርኪናፋሶ ዳኞች በግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ተመለመሉ።
በበርኪና ፋሶ ሀገሪቱን ከሚያስተዳደረው ወታደራዋ ጁንታ ፍላጎት በተቃራኒ እርምጃ የወሰዱ ዳኞች በግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ተመልምለዋል።
በቡርኪና ፋሶ በጁንታው ደጋፊዎች እና በሌሎች ግለሰቦች ላይ በወሰዱት እርምጃ ቢያንስ ስድሰት ዳኞች ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ መመልመላቸውን ሶስት የዳኞች ማህበራት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በፈረንጆቹ 2022 ስልጣን የተቆናጠጠው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ወታደራዊ ጁንታ በብሔራዊ ደህንነት ሽፋን ተቃዋሚዎችን በማፈን እና በግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ክስ ይቀርብበታል።
"የዳኞች ማህበራት እነዚህ ዳኞች በቅርቡ የአሁኑ መንግስት ዋነኛ ደጋፊ ነን የሚሉ ሰዎች ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥተው ነበር" ብለዋል ማህበራቱ።
መግለጫው እንዳለው ፖሊስ በአስገድዶ መሰወር ላይ ምርመራ እንዲያደርግ ትዕዛዝ ያስተላላፉት አቃቤ ህግ እና 60 ሰዎች በሞቱበት የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጠያቂ የሆኑትን ታዋቂ የጁንታው ደጋፊ ባለስልጣን ጉዳይ ያዩት ዳኛ ኢላማ ከተደረጉት መካከል ናቸው።
ወታራዊ አገዛዙ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን እና ሂማን ራይት ዎችን ጨምሮ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት በሚያቀርባቸው ትችቶች ላይ አስተያየት ከመስጠት ሲቆጠብ ይስተዋላል።
የቡርኪና ፋሶ ጦር ጂሀዳዊ አማጺዎች መታየት ከጀመሩበት ከ12 አመታት በፊት ጀምሮ በሳህል ቀጣና ውጊያ እያደረገ ነው። በቀጣናው እየተባባሰ የመጣው ግጭት በቡርኪናፋሶ እና በማሊ መፈንቅለ መንግስት እንዲፈጠር አድርገዋል።
ባለፉት አመታት በምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ሀገራት በርካታ መፈንቅ መንግስታት ተካሂደዋል።