የቡርኪናፋሶ መፈንቅለ መንግስት መሪ ዳሚባ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ
ሙስናን ለመታገል እና የህዝብ አስተዳደርን ከፖለቲካ ለማራገፍም ቃል ገብቷል
ዳሚባ መፈንቅለ መንግስት የፈጸመው በሮክ ካቦሬ የሚመራው መንግስት የእስልማና አማጺያንን ጥቃት ባለማቆሙ ነው ብሏል
የተሳካ መፈንቅለ መንግስት የመሩት የቡርኪናፋሶ ወታደራዊ መሪ ፖል ሄንሪ ዳሚባ ከሳምንታት በኋላ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
ደሚባ በፈረንጆቹ ጥር 24 ቀን ፕሬዚደንት ሮክ ካቦሬን ከስልጣን ያወረደውን ወታደራዊ ጁንታ፤ ካቦሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለውን እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ያስገደደውን የእስልምና አማፂ ቡድን መግታት አልቻሉም በሚል ምክንያት ነው፡፡
- የቡርኪናፋሶ ጦር ፕሬዝዳንቱን ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ
- ኢኮዋስ የቡርኪናፋሶ መፈንቅለ መንግስት" የሀገሪቱን ትልቅ የዴሞክራሲ ውድቀት የሚያመለክት ነው" ሲል አውግዟል
ባለፈው ወር በመንግስት ቴሌቭዥን ቀርበው ስልጣን መያዛቸውን ከማስታወቅ በፊት ብዙም የህዝብ አስተያየት ያልነበራቸው ሌተናል ኮሎኔል፤ ረቡዕ እለት በነበረ ስነ ስርዓት ላይ ንግግራቸውን የከፈቱት ከታጣቂዎች ጋር በተደረገው ጦርነት ለተገደሉት ሰላማዊ ዜጎች እና ወታደሮች የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው፡፡
"...በጠላት ላይ የበላይነት ለመያዝ...መነሳት እና እንደ ሀገር ይህንን ጦርነት ለማሸነፍ ከሚያስፈልገው በላይ እንዳለን እራሳችንን ማሳመን ያስፈልጋል" ብለዋል ደሚባ፡፡
በስለላ አገልግሎቱ እና በመስክ ስራዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የታጠቁ ሃይሎችን በአዲስ መልክ እንደሚያደራጅ እና የሎጂስቲክስ ድጋፍን የበለጠ ተለዋዋጭ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ሙስናን ለመታገል እና የህዝብ አስተዳደርን ከፖለቲካ ለማራገፍም ቃል ገብቷል።
ደሚባ ለምን ያህል ጊዜ ስልጣን ለመያዝ እንዳሰቡ ባይናገሩም ለቀጣናው ኅብረት ከምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) ወደ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲመለሱ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
በቡርኪናፋሶ የተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በፈረንጆቹ ከ2020 ጀምሮ በማሊ፣ ጊኒ እና ቻድ የተካሄደውን ተከትሎ ሲሆን በክልሉ መሪዎች መካከል መፈንቅለ መንግስቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
በማሊ ብጥብጥ የተነሳው መንግስት ከ2015 ጀምሮ በማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር የተስፋፋውን የእስላማዊ ስጋት መቆጣጠር ባለመቻሉ ነው።
ኢኮዋስ ባለፈው ወር በመፈንቅለ መንግስቱ ምክንያት የቡርኪናፋሶን አስተዳደር አካላቶቿን አግዳለች ነገር ግን በማሊ እና በጊኒ ላይ የጣለውን አይነት ማዕቀብ አልጣለም፡፡