
ቡርኪና ፋሶ በቅርቡ በምርጫ ስልጣን የያዙትን መሀመድ ባዙምን በማውረድ ሰልጣን ለተቆናጠጠው የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች አጋርነቷን አሳይታለች
በጁንታ የሚመራው የቡርኪናፋሶ መንግስት በሀገሪቱ ተወዳጅ የሆነው የራድዮ ጣቢያ አዲሶቹን የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች "የሚሰደብ" ቃል ምልልስ ካደረገ በኋላ አግዶታል።
የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ራምታልባ ጂን ኢማኑኤል ኦደራጎ "ተጨማሪ ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ" ራዲዮ ኦሜጋ ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ እንዲታገድ ማድረጋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ለሀገሪቱ ጥቅም ሲባል ይህ አርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።
የኦሜጋ ሚዲያ ግሩፕ አካል የሆነው ራዲዮ ጣቢያው ንብረትነቱ የጋዜጠኛ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው አልፋ ባርይ ነው። የኮሙኒኬሽን ሚኒትስሩ መግለጫ ኬወጡ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነበር የጣቢያው ስርጭት የቆመው።
ራዲዮ ኦሜጋ አርብ እለት እግዱ እንዲነሳ ሁሉንም መንገድ እንደሚሞክር ገልጾ ነበር።
"ውሳኔው ስራ ላይ ያሉ ህጎችን የሚጥስ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ እና የፕሬስ ነጻነት ላይ የተቃጣ ተቀባይነት የሌለው ጥቃት" ነው ብሏል ራዲዮ ጣቢያው ባወጣው መግለጫ።
ጣቢያው እንደገለጸው የእግዱ ትዕዛዝ የመጣው የመንግስት ደጋፊዎች የሆኑ ሰዎች በጣቢያው ሀላፊዎች እና በጋዜጠኞች ላይ የግድ ዛቻ ካደረሱ በኋላ ነው ብሏል።
የሀገሪቱ የጋዜጠኞች ማህበር እግዱ እንዲነሳ ጠይቋል።
ቡርኪና ፋሶ ባለፈው አመት ሁለት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አስተናግዳለች።
ቡርኪና ፋሶ በቅርቡ በምርጫ ስልጣን የያዙትን መሀመድ ባዙምን በማውረድ ሰልጣን ለተቆናጠጠው የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች አጋርነቷን ማሳየቷ ይታወሳል።