አሜሪካ ከተማዋን በሩሲያ መያዟ የጦርነቱን አቅጣጫ እንደማይለውጥ ተናግራለች።
ሩሲያ የዩክሬኗን የማዕድን ከተማ ሶሌዳርን መያዟን ተናገረች
ዩክሬን ጦሯ አሁንም በሶሌዳር ከተማ እየተዋጋች እንደሆነ ብትናገርም ሩሲያ ግን ከተማዋን መቆጣጠሯን አስታውቃለች።
የሶሌዳር መያዝ በወራት ውስጥ የመጀመሪያውና ትልቅ የሩሲያ ስኬት ነው ተብሏል።
ሩሲያ ወታደሮቿ በምስራቃዊ ዩክሬን የሚገኘውን ሶሌዳርን ተቆጣጥረውታል፤ ይህም ለሞስኮ ለወራት ከዘለቀው የጦር ሜዳ የተገላቢጦሽ ስኬት ቢሆንም ኪየቭ ግን ወታደሮቿ በከተማዋ እየተዋጉ መሆናቸውን ተናግራለች።
ሮይተርስ ለቀናት የማያባራ የሩስያ ጥቃት ትኩረት ሆና በቆየችው በሶሌዳር ትንሽ የጨው ማውጫ ከተማ ያለውን ሁኔታ ወዲያውኑ ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል።
ኪየቭ እና ምዕራባውያን የከተማዋን ጠቀሜታ ዝቅ አድርገዋል።
አሜሪካ ከተማዋን በሩሲያ መያዟ የጦርነቱን አቅጣጫ እንደማይለውጥ ተናግራለች።
የሩሲያ የመከላከያ ሚንስቴር ሶሌዳር የተያዘችው በሚሳኤልና በመድፍ መሳሪያዎች በጠላት ላይ ባደረገው የማያቋርጥ የቦምብ ጥቃት ነው ብሏል።
ከተማዋን መያዙ በአቅራቢያ ወደምትገኘው ወደ ባክሙት ከተማ የሚወስዱትን መንገዶች ለመቁረጥ እና የቀሩትን የዩክሬይን ኃይሎች ለማጥመድ ያስችላል ብሏል።
ሞስኮ ባክሙትን ለመያዝ ለወራት ስትሞክር ቆይታለች።
የምዕራባውያን አጋሮች ታንኮችን ወደ ዩክሬን ለመላክ ይወያያሉ መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል።