የእንግሊዙ ካምብሪጅ እንደ አዲስ የመዘገባቸው ዘመን አመጣሽ አዳዲስ ቃላት ምን ምን ናቸው?
አዲስ የተመዘገቡት ከሶስት ሺህ በላይ የእንግሊዘኛ ቃላት ዘመኑ ያፈራቸው ቃላቶች ናቸው ተብሏል
አብዛኞቹ ቃላቶች በኢንተርኔት ዓለም ሰዎች አብዝተው እየተጠቀሟቸው ያሉ እንደሆኑ ተገልጿል
የእንግሊዙ ካምብሪጅ እንደ አዲስ የመዘገባቸው ከ3 ሺህ በላይ አዳዲስ ቃላት ምን ምን ናቸው?
ቃላቶች ከሰው ልጆች ስልጣኔ እና ባህል ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ካምብሪጅ ዲክሽነሪ ወይም መዝገበ ቃላት ደግሞ እንግሊዘኛ ቃላትን በመመዝገብ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ ካምብሪጅ የአሁኑ ዘመን ሰዎች የሚጠቀሟቸው ናቸው በሚል አዳዲስ ቃላትን እና ትርጉማቸውን ይፋ አድርጓል።
እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ በተለይም በኢንተርኔት ዓለም ሰዎች አብዝተው የሚጠቀሟቸው እና አብዛኛው ሰው ይስማማባቸዋል ያላቸውን 3 ሺህ 200 አዲስ ቃላት መመዝገቡንም ገልጿል።
ከተመዘገቡ ቃላት መካከልም አይሲኬኤስ (Icks) አንዱ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙም የሚበላ ምግብ ስብርባሪ አፍ ዳር ሲገኝ ነው ተብሏል።
ሌላኛው አዲስ ቃል ቼፍስ ኪስ ( chef's kiss) አንዱ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙም የአንድ ክስተት በትክክል ሲፈጸም ማለት እንደሆነ ተገልጻል።
ቡፕ (boop) ደግሞ እንደ አዲስ ከተፈጠሩ እና ከተመዘገቡ ቃላቶች መካከል አንዱ ሲሆን አንድን ሰው ወደነው አፍንጫውን አልያም ራሱን በመንካት የምናሳየው ድርጊት ማለት ነው።
ሌላኛው አስገራሚው እና አዲሱ ቃክ በእንግሊዘኛው IFYYK ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙም "ካወከው አወከው ነው" የሚል አቻ ትርጉም ተሰጥቶታል።
"ስፒድረን" አዲሱ ዘመን አመጣሽ ቃል ነው የተባለ ሲሆን ትርጉሙም የኮምፒውተር ጌም ወይም ጨዋታን በፍጥነት የምንጨርስበት መንገድ ነው።
በአንድ ክስተት ላይ ያልተለመደ ስሜትን በፊት ላይ መግለጽ ደግሞ "ፌስ ጆርኒ" ተብሎ እንደ አዲስ መመዝገቡን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።