ከሚስቱ ውጪ ሲወሰልት የነበረው ባል አፕል ኩባንያ ለትዳሬ መፍረስ ምክንያት ሆኗል ሲል ከሰሰ
ግለሰቡ ከሌሎች ሴቶች ጋር የተጻጻፋቸውን መልዕክቶች ሚስቱ እንድታገኛቸው ኩባንያው ተባብሯል ሲል ከሷል
አፕል ሚስጥሬን ባለመጠበቁ ምክንያት የ20 ዓመት ትደሬ ፈርሷል በሚል ኩባንያው 5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ጠይቋል
ከሚስቱ ውጪ ሲወሰልት የነበረው ባል አፕል ኩባንያ ለትዳሬ መፍረስ ምክንያት ሆኗል ሲል ከሰሰ፡፡
ሪቻርድ የተሰኘው እንፈግሊዛዊ ለ20 ዓመት የዘለቀ ትዳር ነበረው፡፡ ይህ ትዳር ባልየው ከሌሎች ሴቶች ጋር ሲወሰልት እንደነበር በሚስት እስከሚደረስበት ጊዜ ድረስ ጤናማ ነበር ተብሏል፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ይህ ሪቻርድ የተባለው (ስሙ የተቀየረ) ሰው የአፕል ስልክ ተጠቃሚ ሲሆን ከሚስቱ ውጪ ከሌሎች ሴቶች ጋር ያደረጋቸውን መልዕክቶች ሚስቱ እንዳታየው በሚል ተከታትሎ በየጊዜው ሲያጠፋ ቆይቷል፡፡
ለዓመታት በዚህ መንገድ የዘለቀው ይህ ባል አንድ ቀን ግን ሚስቱ በቤቱ ውስጥ የሚጠቀሙበትን የአፕል ታብሌት ስትከፍት ባሏ ከሌሎች ሴቶች ጋር ያደረጋቸውን የመልዕክት ለውውጦች ታያለች፡፡
ለዓመታት ባሏ ሲወሰልትባት እንደነበር የተረዳችው ሚስትም ፍቺ ትጠይቃለች፡፡
የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሴት ልጅ ባል እንድታገኝ ተጸለየላት
መልዕክቴን እየተከታተልኩ ሳጠፋ ብቆይም ኩባንያው ግን መልዕክቶቹን በዘላቂነት ሳያጠፋ ቆይቶ ሚስቴ እንድታየው እና ለትዳሬ መፍረስ ምክንያት ሆኗል ሲል ወቅሷል፡፡
አፕል ኩባንያ የደንበኞቹን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል ያለው ይህ እንግሊዛዊ ኩባንያው 5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ክስ እንደመሰረተ ዘ ታየምስ ዘግቧል፡፡
ሪቻርድ ለዚህ ሚዲያ እንዳለው የተለዋወጥኳቸውን መልዕክቶች ሳጠፋ አፕል ኩባንያ ይህ መልዕክት ከዚህ ስልክ ላይ ብቻ ጠፍቷል ቢለኝ ኖሮ በሌሎች መጠቀሚያ ላፕቶፕ ላይ ሄጄ አጠፋ ነበር ስለዚህ ተጠያቂው ኩባንያው ነው ብሏል፡፡
ክስ የቀረበበት የአፕል ኩባንያ እስካሁን ለቀረበበት ክስ ምላሽ እንዳልሰጠ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡