ቻይና የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ለመፍታት የሰላም እቅድ ማውጣቷ ይታወሳል
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሩሲያ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚነጋገሩ ሁለቱ ሀገራት አሳውቀዋል።
የሩሲያው ፓትሪያርክ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ባላት ቤተክርስቲያን ላይ የምትፈጥረውን ተጽእኖ እንድታቆም ጠየቁ
በሁለቱም ወገኖች "ሞቅ" ያለ አቀባበል የተደረገለት የዩክሬን ጦርነት የሚያስቆም እቅድ ማውጣቷ ይታወሳል።
የዢ የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ (መጋቢት 10 እስከ 11) ጉዞ፤ ቻይና ባለፈው ወር "የዩክሬን ቀውስን ለመፍታት" ባለ 12 ነጥብ እቅድ ካወጣች በኋላ እና አንድ ከፍተኛ የቻይና ዲፕሎማት ለዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለድርድር ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ነው ።
የሰላም እቅዱ የንጹሃንን ጥበቃ እና ሩሲያና ዩክሬን አንዳቸው የሌላውን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ ይጠይቃል።
ይሁን እንጂ አሜሪካ እና ኔቶ ቤጂንግ ጦርነቱን ከማውገዝ በመቆጠቧ ለሽምግልና የምታደርገው ጥረት ተአማኒ አይደለም ብለዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን እንዳሉት ከአራት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የሆነው የዢ ሩሲያ ጉብኝት፤ በከፊል "ሰላምን" ለማስፋፋት ነው።
ምንም እንኳ ቃል አቀባዩ የዩክሬንን ጦርነት በግልጽ ባይጠቅሱም።
መሪዎቹ በዋና ዋና አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ እንደሚለዋወጡ፣ የሁለትዮሽ መተማመንን እንደሚያጠናክሩ እና የኢኮኖሚ አጋርነታቸውን እንደሚያጎለብቱ ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።