የቻይና እና የሩሲያ መሪዎች በኢንዶኔዥያው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ሊካፈሉ ነው
የኢንዶኔዥያው ፕሬዝዳንት የዩክሬን እና ሩሲያን ጦርነት ለመፍታት ጥረት እያደረጉ ነው
በኢንዶኔዥያው ስብሰባ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል
የቻይና ፕሬዝደንት ዢ ጅንፒንግ እና የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በመጭው ህዳር ወር በሚካሄደው የኢንዶኔዥያው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ሊሳተፉ ነው፡፡ ሮይተርስ የኢንዶኔዥያ ፕሬዝደንት ጆኮ ዊዶዶ አማካሪን ጠቅሶ እንዘገበው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ስብሰባውን ይካፈላሉ፡፡
አማካሪው ኢዲ ዋድጃጃንቶ ሁለቱ መሪዎች እንደሚገናኙ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
የናሽናል ሬዚለንስ ኢንስቲቲዩትን የሚመሩት ዊድጃጃንቶ ፕሬዝደንቱ ሁለቱ መሪዎች ወደ ኢንዶኔዥያ ባሊ ከተማ መጥተው ስብሰባውን እንደሚያካሄዱ ነግረውኛል ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ጆኮ ዊዶዶ ቀደም ሲል ሁለቱ መሪዎች በቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ እንደሚካፈሉ ለብሉምበርግ አረጋግጠዋል፡፡
ሮይተርስ መሪዎቹ ስለመሳተፋቸው ከሩሲያ ሆነ ከቻይና ምላሽ አለማግኘቱን ዘግቧል፡፡
በቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ ላይ የዩክሬኑ መሪ ዘለንስኪ ተጋዘብዋል፤ የኢንዶኔዥያው ፕሬዝደንት ጆኮ ዊዶዶ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ያለውን ግጭት በሽምግልና ለመፍታት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
በኢንዶኔዥያው ስብሰባ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሚሳተፉ ሲሆን ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ይገናኙ ወይም አይገናኙ የታወቀ ነገር የለም፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት፣ ሩሲያ አሜሪካን ጨምሮ ከምእራባውያን ጋር ወታደረዊ ፍጥጫ ውስጥ የገባች ሲሆን ቻይና ደግሞ በታይዋን ጉዳይ በተለይም ከቻይና ጋር ወደታራዊ ትብብር እስከማቋረጥ የደረሰ ቅራኔ ውስጥ ገብታለች፡፡