ለሰዓታት ብቻ በህይወት ይቆያሉ የተባሉት ህጻናት ሰባተኛ ዓመታቸውን አከበሩ
ህጻናቱን በቀዶ ትገና ማላቀቅ የሚቻል ቢሆንም በህይወት መቆየት የሚችሉት ግን አንዳቸው ብቻ ይሆናል ተብሏል
ወላጆቻቸው አንድኛዋን ለማዳን አንድኛዋን እንድትሞት መፍረድ አንችልም በማለታቸው ህጻናቱ አሁንም ተጣብቀው አሉ
ለሰዓታት ብቻ በህይወት ይቆያሉ የተባሉት ህጻናት ሰባተኛ ዓመታቸውን አከበሩ፡፡
ተጣብቀው ከተወለዱ በኋላ ለሰዓታት ብቻ በህይወት ይቆያሉ የተባሉት መንታ ህጻናት ሰባተኛ የልደት በዓላቸውን አክብረዋል፡፡
ማርሜ እና ንዴዬ የተባሉት እነዚህ ህጻናት በሴኔጋል ዳካር የተወለዱ ሲሆን ወደ ብሪታንያ የመጡት በቀዶ ጥገና ለማላቀቅ በሚል ነበር፡፡
ይሁንና ለንደን የሚገኘው የቀዶ ጥገና ሆስፒታል ህክምናውን ማድረግ እንደሚችል ነገር ግን አንድኛቸው ብቻ በህይወት ሊቆዩ ይችላሉ ማለቱን ተከትሎ ህክምናው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡
ብሪታንያ 22 ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ስትቀያየር የተመለከቱት የ104 አመት መንትዮች
የህጻናቱ ወላጆች የግድ አንድኛቸውን መምረጥ እንዳለባቸው ሲነገራቸው ቀዶ ህክምናው እንዲቋረጥ መወሰናቸውን ተናግረዋል ተብሏል፡፡
አባታቸው ኢብራሂም ለቢቢሲ እንዳለው በ2017 ቀዶ ህክምናውን ለማድረግ ወደ ለንደን እንደመጣ ፣ ነግር ግን ሐኪሞች የነገሩት ነገር እንዳስደነገጠው እና ለውሳኔ መቸገሩን ተናግሯል፡፡
አንድኛቸውን ለማዳን የግድ አንድኛቸው መሞት አለባቸው ስባል ይህንን መምረጥ እቸገራለሁ ይህ የፈጠራቸው ፈጣሪ ውሳኔ መሆን አለበት ብዬ ህክምናው እንዲቀር አድርጌያለሁ ብሏል፡፡
እነዚህ ህጻናት የየራሳቸው ልብ፣ የራስ ቅል እና የጀርባ አጥንት ያላቸው ሲሆን እግራቸው ግን ሁለት ብቻ ነው፡፡
የመንትዮች ተጣብቀው መወለድ የሚያጋጥም እንደሆነ የሕክምና ባለሙያዎች የሚናገሩ ሲሆን በ500 ሺህ መንትዮች መካከል በአንዱ ላይ ሊከሰት ይችላልም ተብሏል፡፡