የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መፈረም ባጠናቀቅነው ዓመት ውስጥ ከነበሩ አበይት ክስተቶች መካከል ዋነኛው ነበር
በ2015 ዓ.ም የነበሩ አበይት ክስተቶች ምን ምን ነበሩ?
የ2015 ዓ.ም ዓመት ሁላችንም በምናውቀው መልኩ ተጠናቋል፡፡ ዓመቱ የተለያዩ አበይት ክስተቶችን አስተናግዶ ያለፈ ሲሆን አልዐይን በዓመቱ የነበሩ ዋና ዋና የሀገር ውስጥ እና የውጭ ክስተቶችን እንደሚከተለው አሰናድቶላችኋል፡፡
ከሀገር ውስጥ ከነበሩ የአመቱ አበይት ክስተቶች መካከል ለሁለት ዓመታት ያህል ደም አፋሳሽ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ያስቀረው የሰላም ስምምነት ዋነኛው ነበር፡፡
ይህ ስምምነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በትግራይ ሀይሎች እና በፌደራል መንግስት መካከል የተፈረመ የሰላም ስምምነት ነው፡፡
ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ማጠናቀቋን ተከትሎ ግብጽ ምን አለች?
በቀድሞው የደቡብ ክልል ስር በነበሩ አካባቢዎች የህዝበ ውሳኔ መደረጉን ተከትሎ አዳዲስ ክልሎች መዋቀራቸው ሌላኛው የ2015 ክስተት ነበር፡፡
የተማከለ የጸጥታ ሀይል ማዋቀር በሚል የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሶ ማደራጀት ጉዳይ ሌላኛው የዓመቱ አበይት ክስተት ሲሆን ይህን ተከትሎ በአማራ ክልል ሌላ ደም አፋሳሽ ጦርነት መከሰቱ የዓመቱ አበይት ክስተት ነው፡፡
ከአዲስ አበባ የተወሰኑ ቦታዎችን በመያዝ እና በቀድሞ ስሙ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን በሚል ይታወቅ የነበረው አስተዳድር ሸገር ከተማ አስተዳድር በሚል መዋቀሩ ሌላኛው በ2015 ዓ.ም ያስተናገድነው አበይት ክስተት ሆኗል፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ እና የትግራይ ቤተ ክህነት እናቋቁም በሚል የተነሱ ጉዳዮች እና ተያያዝ ክስተቶች ሌላኛው ከአበይት ክስተቶች መካከል የሚጠቀስ ነበር፡፡
ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልል በሆነው የሸገር ከተማ ስር የተፈጸሙት የመኖሪያ ቤት እና ማምለኪያ ስፍራዎች ፈረሳ የዚሁ አበይት ክስተት አንዱ አካል ነበሩ፡፡
ወጪው እስከ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል የተባለው የአዲስ ቤተ መንግስት ግንባታ ወይም የጫካ ፕሮጀክት በ2015 ዓም ከነበሩ አበይት ክስተቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡
የሳፋሪኮሙ ኤምፔሳ የበይነ መረብ መገበያያ ስርዓት ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ማግኘቱ እና ስራ መጀመሩ ሌላኛው ያጠናቀቅነው ዓመት አበይት ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡
ኢትዮጵያ የብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ጥምረት የሆነው ብሪክስን መቀላቀሏ ከአበይት ክስተቶች መካከል ሌላኛው ተጠቃሽ ክስተት ነው፡፡
በኢትዮጵያ የ2012 ዓ.ም አበይት ክስተቶች ምንድን ናቸው?
በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ እና አራተኛው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ መሙላት ሌላኛው በዓመቱ ከነበሩ ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ነበሩ፡፡
በኢትዮጵያ በተፈጠረው የፖለቲካ ትኩሳት ጋር በተያያዘ የፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እስር በሀገር ውስጥ ከተፈጠሩ አበይት ክስተቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ከዓለም አቀፍ ጉዳዮች መካከል ደግሞ በጎረቤት ሀገር ሱዳን የተከሰተው ጦርነት፣ በመካከለኛው እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት የተፈጸሙ መፈንቅለ መንግሥታት በተጠናቀቀው ዓመት የተፈጸሙ ክስተቶች ነበሩ፡፡
አፍሪካ ህብረት የቡድን 20 አባል መሆን፣ ብሪክስ አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉ፣ የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት አሁንም እልባት አለማግኘቱ፣ የቱርክ ሶሪያ እና ሞሮኮ የመሬት መንቀጥቀጥ እንዲሁም በኳታር አስተናጋጅነት የተካሄደው የፊፋ አለም ዋንጫ በ2015 ዓ.ም ከነበሩ አበይት ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ነበሩ፡፡
በእርስዎ አስተያየት በ2015 ዓ.ም አበይት የሚሉት ክስተት የትኞቹ ናቸው?