ስፖርት
በፓሪስ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ያገኙ ሀገራት እነማን ናቸው?
ስድስት የዓለማችን ሀገራት በኦሎምፒክ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሜዳሊያ አግኝተዋል
አፍሪካዊያኑ ቦትስዋና እና ኬፕ ቨርዴ በታሪክ የመጀመሪያቸውን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ በፓሪስ ካገኙ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
በፓሪስ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ያገኙ ሀገራት እነማን ናቸው?
ለ17 ቀናት የቆየው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ባሳለፍነው እሁድ ምሽት መጠናቀቁ ይታወሳል።
በአሜሪካ የበላይነት በተጠናቀቀው በዚህ ውድድር ላይ ከ206 ሀገራት የተውጣጡ ከ10 ሺህ በላይ አትሌቶች ተሳተፈውበታል።
በዚህ ውድድር ላይ ከተሳተፉ ሀገራት መካከል 91 ያህሉ ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል።
ሜዳሊያ ካገኙ ሀገራት መካከል ስድስቱ ሀገራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
ቦትስዋና እና ኬፕቨርዴ በታሪክ የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ካገኙ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ሴንት ሊውስ፣ ዶምኒካ፣ ጓቲማላ እና አልባኒያ በፓሪሱ ኦሎምፒክ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ሜዳሊያ ካገኙ ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል።
አሜሪካ በ40 የወርቅ፣ 44 የብር እና 42 የነሃስ ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።